[ / / / / / / / / / / / / / ] [ dir / random / 93 / biohzrd / hkacade / hkpnd / tct / utd / uy / yebalnia ]

Catalog (/ethiopiaoneamhara/)

[Create a thread]
Sort by: Image size: [Show all]
R:0 / I:0 / P:1 [R] [G] [-]

የአማራ ፋኖ በጎጃም መግለጫ የ ድማማ ዴክላሬሽን

'ከአማራ ፋኖ በጎጃም" የተሰጠ መግለጫ

(ድማማ ዲክላሳሬሽን)

የአማራ ሕዝብ በፋሽስቱ የብልጽግና ስርዓት በተደቀነበት የህልውና አደጋ እና ከተከፈተበት ሁሉን አቀፍ ጥቃትና ወረራ ራሱን ከመከላከል ወደ ተሟላ በትጥቅ ትግል የሚደረግ ጠላትን ማሸነፍ፤ በመላው ኢትዮጵያዊያን ፈቃድ የሚመሰረት አዲስ ስርዓት ለማዋለድ በከፍተኛ የድል ግስጋሴ ላይ መሆኑ ታዉቆ ያደረ ጉዳይ ነው፡፡ ይህንንም በከፍተኛ የእሳቤ እና ድርጀታዊ ጥንካሬ መምራት በውል እየተተገበረ እና በሚመጥን መልኩ እየተጠናከረ እየሄደ ያለ ነው፡፡

ትግሉ አሁን ባለበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ የአምበሳውን ድርሻ እየተወጡ ያሉ የፋኖ አደረጃጀቶች የዓላማ እና የተልዕኮ ልዩነት ባይናራቸውም አንድ ወጥ መዋቅራዊ ቅርፅ መያዝ አለመቻላቸው በትግሉ ሂደት እና ፍጥነት ላይ የፈጠረው ሳንካ በቀላሉ የሚታይ አለመሆኑን በትግሉ ዛሂደት ከገጠሙን ችግርች መረዳት ችለናል፡፡

የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ከተመሰረተበት ዕለት ጀምር' ባከናወናቸው ተጋድሎዎች ደማቅ ታሪክ የጻፈፊ ሲሆን የፋኖን እንቅስቃሴ በማሰልጠን፤ በማደራጀት፤ ማስታጠት እና ማታገል ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ የአማራ ሕዝብ ተጋድሉ እና የፋኖ ሠራዊት እድገት የወለደው የጎጃዛም እዝ ፋኖም ትግሉን ወደ ከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ረገድ ያደረገው አስተዋፅኦም በታሪክ ፊት የሚታወስ ነው፡፡

አሁን ባለንበት ነባራዊ ሁኔታ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ እነኝህን ስሞች መጠቀም አስፈለጊ ሆኖ አለመገኘቱን እና ትግሉን በተቀናጀ የአመራር ስምሪት መምራት እና ለዚህም መገዛት የሚገባን ስለመሆኑ የህዝባዊ ኃይሉም ሆነ የእዙ አመራሮች ከተደጋጋሚ ውይይቶች በኋላ በሙሉ ድምፅ አምነንበታል።፡ ይህንንም ስምምነትና ውሳኔ "ድማማ ዲክላሬሽን" በሚል ሰይመነዋል፡፡

ይህንን የአደረጃጀት ጉዳይ እልባት ለመስጠት የተለያዩ ወገኖቻችን ከሚያደርጉት ጥረት ጎን ለጎን እኛም ለሶስት ግዜያት ያህክል ፍፁም ወንድማማችነት፤ አማራዊ ጨዋነት እና ኢትዮጵያዊ ግብረ ገብነት በተላበሰ መልኩ ባደረግነው ውይይት መሰረት አንድ መዋቅር እና አመራር የሚፈጠርበትን

ሁኔታ ለማምጣት ተስማምተናል፡፡

ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረስነው ትግሉ የደረሰበት ደረጃ፤ ቀጣይ የሚጠበቅብን ከፍተኛ ኃላፊነት፤ ይህንን ትግል የተሻለ ደረጃ ላይ ደርሶ ማዬት የሚፈልጉ የፋኖ ሰራዊት አባላት፤ ሌሎች አቻ

የፋኖ አደረጃጀቶች፤ በውጭ እና በሀገር ውስጥ ያሉ ደጋፊዎች ለጉዳዩ ያላቸውን ጉጉት እና ፅኑ ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት የሁለቱም ወገን አመራርች በአንድነት የሚመሩትን የፋኖ አደረጃጀት ማምጣት እጅጉን አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ ነው፡፡

በዚህም መሰረት "የአማራ ፋና በጎጃም" በሚል መጠሪያ ወደ አንድና ወጥ የፋና አደረጃጀት ማሳደጋችንን ለመላው የሰራዊት አመራርና አባላት፤ ለመላው የአማራ ህዝብ እና ኢትዮጵያዊያን

አንዲሁም ደጋፊዎቻችን ሁሉ ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው።፡

በመሆኑም "የአማራ ፋኖ በጎጃም" ቀጥሉ የተዘረዘሩትን ጥሪዎች ያቀርባል፡-

1/ ይህ መግለጫ ከተሰጠበት እለት ጆምሮ በነባር አደረጃጆቶች ስር የሚንተሳተሰው የፋኖ ሰራዊት

“የአማራ ፋኖ በጎጃም” አመራር እና አባል መሆኑን አውቆ በዚሁ መጠሪያ እንዲጠቀም እያሳሰብን ማዲያዎችም ከዚህ ዕለት ጀምሮ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል እና የጎጃም እዝ ፋኖ የሚሉትን አጠራሮች እንዳይጠቀሙ በዚህ ፋንታ "የአማራ ፋኖ በጎጃም" የሚለውን ስም ብቻ እንዲጠቀሙ እናሳስባልን፡፡

2/ አንድ መዋቅር እና አመራር ለመፍጠር በተደረገው ውሳኔ መሰረት የአማራ ፋኖ በጎጃም አመራሮች;

1. አርበኛ ዘመነ ካሴ - ሰብሳቢ፤

2. ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው - ም/ሰብሳቢ እና ወታደራዊ አዛዥ

2.1. ሻለቃ የኔዓለም ዘለቀ - ም/ወታደራዊ አዛዥ

22. ዘመቻ ኃላፊ - መ/አ አበበ ሰው መሆን

23. ም/ዘመቻ ኃላፊ - መ/አ ማርቆስ አሞኘ

2.4. ስልጠና ኃሳፊ - ፃ/አ ታዬ ብርሐኑ

2.5. ም/ስልጠና ኃላፊ - ኮ/ል ጌታሁን መኮንን

2.6. ሎጀስቲክስ ኃላፊ - ዘመነ- ገረመው

2.7. ም/ሎጀስቲክስ ኃላፊ - መንበሩ ጌታዬ

2.8. ወታደራዊ አስተዳደር - ዛ/አ ይበልጣል መልካሙ

3. አርበኛ እና ጠበቃ አስረስ ማረ ዳምጤ - ም/ሰብሳቢ እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ

3.1. ግሩም ምሳሌ - ም/የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ

4. የውጭ ግንኙነት እና የዲያስፖራ ጉዳዮች መምሪያ -

4.1. ስሜነህ ሙላቱ - ኃላፊ

4.2. ኃ/ሚካኤል ባዬ - ም/ኃላፊ

5. የቀጠናዊ ትስስር መምሪያ -

5.1. የቆዬ ሞላ - ኃላፊ

5.2. አዲሱ ፈጠነ - ም/ኃላፊ

6. የህዝብ ግንኙነት መምሪያ

6.1. ማርሸት ፀሐው - ኃላፊ

6.2. ዮሐንስ አለማየሁ - ም/ኃላፊ

7. ስትራቴጂክ ጉዳዮች መምሪያ

7.4. ተሰማ ካሳሁን - ኃላፊ

7.2. ጎበዜ ጌታሁን - ም/ኃላፊ

8. የፋይናንስ እና ንብረት አስተዳድር መምሪያ

8.1. ማንችሎት እሱባለው - ኃላፊ

8.2. ዳኛው ሽባባው - ም/ኃላፊ

9. የ፳/ቤት ኃላፊ

9.1. ይትባረክ አንዳርጌ - ኃላፊ

9.2.- በለጠ አብርሐም - ም/ኃላፊ

10. የአደረጃጀት ዘርፍ መምሪያ

10.1. አሸቱ ጌትነት - ኃላፊ

10.2. ስለሺ ከበደ - ም/ኃላፊ

11. መረጃ እና ደህንነት መምሪያ - xxx

ሆነው እንዲመሩ ተስማምተናል፡፡

3/ ይህ መግለጫ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ' የሚሰበሰብ የሉጅስቲክስ እና የፋይናንስ ድጋፍ “የአማራ ፋኖ በጎጃም" በሚሰጠው መመሪያ እና ለዚሁ ጉዳይ በሚያደራጀው መምሪያ (የስራ ክፍሎች) መሰረት እንዲፈፀም እና በዚህ አግባብ እንዲከናወን መወሰናችንን እናስታውቃለን፡፡ ሁሉም መዋቅራዊ ጉዳይ በተመሳሳይ አካሄድ የሚፈፀም ይሆናል፡፡

4/ ለመላው የአማራ ህዝብ እና ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በዚህ ውሳኔያችን መሰረት ኃይላችንን በማጠናከር ለምንፈጽመው ከፍተኛ ጠላትን የማሽመድመድ እና ወደ ድል የመገስገስ ሂደት በሙሉ ልብ እና ቀና ፍላጎት ከጎናችን በመሰለፍ ይህንን ሀገር እና ህዝብ ጠል ጥገኛ ፋሽስት ስርዓት በማስወገድ ለፍትሕ እና እኩልነት የቆመ አዲስ ኢትዮጵያዊ ስርዓት ለመመስረት ዝግጁ እንድትሆኑ ብርቱ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

5/ በሌሎች የአማራ ክፍለ ግዛቶች እና ቀጠናዎች ያላችሁ የፋኖ አደረጃጀቶች እንደ አንድ አማራ ልንሰራ ያቀድነውን እና እየደከምንበት ያለውን አንድ ወጥ ደርጅት ለመፍጠር ለምናደርገው ርብርብ እና ወንድማዊ ጥሪ ራሳችሁን አንድታዘጋጁ እና በፍጥነት የጋራ ቤታችንን እንድንቀልስ

ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ይህም የትግላችን ወሳኙ ምዕራፍ ነው፡፡

6/ ለትግሉ አበርክቶ ያለው የተለያየ አቅም፤ ሙያ እና ፍላጎት ያላችሁ ምሁራን ያለንበትን የህልውና ትግል መቀላቀል ታሪካዊ የውዴታ ግዴታችሁ መሆኑን ተገንዝባችሁ እና ድርጅታችን

አቅም እና ፍላጎቱ ያለውን ሁሉ የሚያስተናግድበት መደላድል እንዳለም አውቃችሁ ትግሉን እንድተቀላቀሉ እናሳስባለን፡፡

7/ በመጨረሻም ትግላችን የደረሰበትን ደረጃ በውል መገንዘብ እንደሚገባ እየገለጽን ይህ አደረጃጀት የምንታገልለትን ህዝብ፤ የትግሉን ደጋፊዎች፤ የሰራዊታችንን ወቅታዊ ፍላጎት በአጠቃላይ ጊዜው የጠየቀውን የመዋቅርና አመራር ማጠናከር ታሳቢ አድርገን በቅንነት ያዋለድነው አደረጃጀት መሆኑን የሚመለከተው ሁሉ እንዲረዳው እና ከጎናችን እንዲቆም ጥሪ እናቀርባለን፡፡

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!

ድል ለአማራ ሕዝብ!

የካቲት 15/2016 ዓ.ም

ግሽ ዓባይ - ጎጃም፤ ኢትዮጵያ

R:0 / I:0 / P:1 [R] [G] [-]

እናት ለልጆቿ አማራ ፋኖ

R:0 / I:0 / P:1 [R] [G] [-]

ከጎጃም ዕዝ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ !! ታህሳስ 08/2016 ዓ.ም

የአማራ ህዝብ እየታገለ ያለው ለህልውናው ነው። ይህን ስንል በአማራ ህዝብ ላይ በአለም ታይቶ ማይታወቁ አሰቃቂ ግፎች ተፈጽመውበታል። ለምሳያ ያክል፦ ከነፍስ ወከፍ እስከ ጅምላ የዶዘር ቀብር፤ ህፃናትን ከመቆራረጥ እስከ የእናት ሆድ መሰንጠቅ፤ ከእምነት ተቋማት መውደም እስከ አባቶች መቃጠል፤ ከተማሪዎች መታገት፣ ሰነድ መቃጠል፣ መደፈር፣ከፎቅ መወርወር እስከ አሰቃቂ ግድያዎች፣ ተንቀሳቅሶ መስራት ማይቻልበት፣ ሾፌሮች የሚታገቱበት አለፍ ሲልም በአማራነታቸው የሚታረዱበት፣ በአማራነቱ በየቦታው የሚፈናቀልበት፣ የልማት ጥያቄና መማር ቅንጦት የሆነበትና እንደህዝብ መጥፋት አለበት ተብሎ ተፈርጆ መዋቅራዊ በሆነ መንገድ ለመጨፍጨፍ የተዘመተበት ህዝብ ነው። ስለዚህ የአማራ ህዝብ የሚታገልለት ጽኑ የሆነ አላማና ግብ አለው።

የጎጃም ዕዝ ያወጣውን ሶስተኛውን መግለጫ ዕዙ ሳይሆን ከዕዙ ውጭ የሆነ አካል ፅፎ የላከው ነው በማለት የሚዲያ ዘመቻ የከፈቱና ያስከፈቱ አካላት መሬት ላይ ያለውን ነባራዊ እውነት ያልተረዱ መሆናቸውን የተገነዘብን ሲሆነ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እያሳሰብን የጎጃም ዕዝ በውጭም ሆነ በውስጥ የራሱ ባልሆኑ ሀይሎች የማይዘወር እና የአማራ ህዝብ ትግል በወለዳቸው፤ ከጎጃም ማህፀነ ለምለም እናቶች በተገኙ፤ በእሳት ቀለበት እየተራመዱ ትግሉን በሚመሩ በአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች የሚመራ መሆኑን ማሳወቅ እንፈልጋለን። በመሆኑም የተወሰኑ ውይይቶች ጥሪያችንን ከተቀበሉ የቀድሞ አደረጃጄቶች ጋር የተጀመረ ሲሆን ችግር ፈቺ የሆነ ቀጠሮ የተያዘ መሆኑን እየገለጽን ዉጤታማ እንዲሆ የተለያዩ ስራዎች ተጀምረዋል። በመሆኑም የአማራ ፋኖ ይህን ጨፍጫፊ ስርዓት ማስወገድ የመጀመሪያ መፍትሄ አድርጎ አገረ መንግስትን የመስራት ጥበብ ከሌላ አጋር ኢትዮጵያውያን ጋር የራሱን አሻራ እንደሚያስቀምጥ ጥርጥር የለንም እያልን ዕዙ ባንዳንድ ጉዳዮች ከተወያዬ በኋላ ይህን ባለ 3 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

1ኛ, እጃችሁን እንድትሰጡ ብሎ አሸባሪውና ጨፍጫፊው መንግስት በሚዲያ ላይ ባወጣው መግለጫ ይህ የሀይል ሚዛንን ለይቶ የማያውቅ፣ ለአማራ ህዝብ ያለውን ንቀትና የአማራ ፋኖ የሚታገልለትን አላማና ግብም ለወንበራቸውና ለእኩይ አላማቸው ፈፅሞ ጠር እንደሆነባቸው ያሳዬ መግለጫ ነው። በመሆኑም ከአማራ ፋኖ ጋር የገጠማችሁ እና ከሞት የተረፋችሁ በየቦታው በግዴታ ታፍሳችሁ የመጣችሁ እና በሙስናና በማጭበርበር የተዘፈቀው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምክንያት በድህነት የጣራ ወለል በታች ሁናችሁ እንደ ስራ እድል ቆጥራችሁና አላማው አገርን መጠበቅ ነው በሚል ቅንነት ተቀላቅላችሁ የነበርና በሴራ ውጊያ ከሞት የተረፋችሁ ውስን ሃይሎች የጨፍጫፊው መንግስት ስልጣን አስጠባቂ ከመሆን ወጥታችሁ ብሄር ሳይመርጥ ምርኮኞችን ለሚንከባከበው ፍኖ እጃችሁን እንድትሰጡ ስንል በጥብቅ እናሳስባለን።

2ተኛ, የሀገሪቱ ከፍተኛው የጦር ባለስልጣን የሰጠው መግለጫ ለአማራ ህዝብ ያለውን ጥላቻ በግልጽ ያሳየበት ንግግር ከበቂ በላይ ነው። ድሮኑን ከበቂ በላይ እንደተጠቀመበት በበቂ ሁኔታ ባልተጠበቁ የከሰሩ የመዘለባበድ ንግግሮቹ አስቀምጧል። አሸባሪው ሀይል ፋኖን በድሮን ደበደበ የሚል መግለጫም አላወጣንም ትጥቅ ይዞ እየተዋጋ ያለውን የአማራ ፋኖ አንገት ማስደፋት የሚችል አቅምም ስነልቦናም የላቸውም። ይህ ደግሞ ከክላሽኮቭ እስከ ዙ-23 ያስታጠቀን የአሸባሪው ስልጣን አስጠባቂ መሆኑ በቂ ምስክር ነው። የአማራ ፋኖ በድሮንና ከባድ መሳሪያ ህፃናትን፣ አዛውንቶቾን፣ የእምነት ተቋማት አባቶችንና ሰብል በመሰብሰብ ላይ ያሉ አርሶ አደሮችን በአጠቃላይ ንፁሃንን እየደበደበ መሆኑን ብናሳውቅም አማራ እንደ ህዝብ መጥፋት አለበት የሚለውን እቅድ በአደባባይ ምስክርነት የሰጠበትን እና አቅም ያነሰው ይህ ቡድን ንፁሃንን መጨፍጨፉን እንደሚቀጥል በአደባባይ ምስክርነት ሰጥቷል። ሚዲያ የሌለው ህዝብ ሰሚም ሆነ አልቃሽ እንደሌለው ጠንቅቀን እናውቃለን። በመሆኑም የትግሉ አጋር የሆናችሁ የሀገራችን ህዝቦች እና የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በሙሉ በህዝባችን ላይ የተቃጣውን ጥቃት እንዲያውቅልን ስንል እያሳሰብን ይህን አለም አቀፍ የጦር ወንጀል በማሳወቅ ከጎናች እንድትሆኑ ስል እውነትን ለሚደፍር ሚዲያዎች፣ የሰባዊ መብት ተሟጋቾች እና ለሁሉም ማህበረሰብ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

3ተኛ, የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ በተመለከተ የለት ጉርሳቸውን በዚህ እንቅስቃሴ ላይ ላደረጉነ ሰብል ለመሰብሰብ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አስፈላጊ በመሆኑና መንገድ ላይ የቆሙ መኪኖችን ግምት ውስጥ በማስገባት ላልተወሰነ ጊዜ እንቅስቃሴ የተፈቀደ መሆኑን እየገለጽን የጨፍጫፊው ሃይል ሸቀጣሸቀጦች ስንዴን ጨምሮ መድሃኒቶች ወደ አማራ *ክልል እንዳይገባ ትእዛዞች መሰጣታቸው ይታወቃል። ስለዚህ በተቃራኒው ከክሰል እስከ ማርና ቅቤ፣ ከስንዴ እስከ ጤፍ ከፍተኛ በጀት ተመድቦ እየገዙ ሲሆን አላማውም ጦርነትን በማራዘም የአማራን ህዝብ በርሃብ አለንጋ እንዲገረፍና በኢኮኖሚው እንዲዳከም በመዋቅራዊ መንገድ ታቅዶበት እየሰሩ መሆናቸውን በባለፈው መግለጫችን ማስታወቃችን አይዘነጋም። ስለሆነም የጨፍጫፊው ስልጣን ጠባቂ የሆነው ሀይል እጁን መስጠት የሚፈልግ እጁን እስኪሰጥ እና የተራረፈው በአማራ ፋኖ እስኪደመሰስ ድረስ ምንም አይነት ጭነት ከአማራ *ክልል ወደሌላ ቦታዎች ጭኖ መውጣት የማይቻል መሆኑን እያሳሰብን ይህን አድርጎ በተገኜ ግለሰብም ሆነ ተቋም በየትኛውም የጎጃም አካባቢ በሚገኙ ለዕዙ አደረጃጀቶች ውርስ ተደርጎ ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ በማከፋፈል የተተኳሽ መግዣና ለትግሉ እንዲውል ትእዛዝ የተላለፈ መሆኑን በአፅኖት እንገልፃለን።

ከእውነት ጋር የቆመ ህዝብ ያሸንፋል!!

ድል ለተገፋው የአማራ ህዝብ!!

ድል ለፋኖ!!

የጎጃም ዕዝ ፋኖ!

ታህሳስ 08/2016 ዓ.ም

R:0 / I:0 / P:1 [R] [G] [-]

ከአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ የዕዙን መመስረት አስመልክቶ

የተሰጠ መግለጫ

ታህሣሥ 03/2016 ዓ.ም

ደ/ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ወገልጤና ከተማ

የኢትዮጵያ ማህበረሰባዊ የለውጥ ሂደት ታሪክ ማለትም የሀገረ መንግስት ምስረታና ግንባታ ስርአት፣ ማህበራዊ መስተጋብርና ትስስር ስርአት ፣የምረተ-ስልት ስርዓት እና የእውቀት ምንጭና ስርጸት ስርዓት እንደሚያሰገነዝበው የኢትዮጵያ መገለጫዊ ማንነት የ60ዎቹ ትውልዶች እንዳቀነቀኑትና የአሁናዊ ስርዓት መተክል ሆኖ እያገለገለ እንዳለው የአንድ ማሕበረሰብ ነጠላ ማንነት አልነበረም ፡፡ የልቁንም የሀገራችን መገለጫዊ ማንነት ከሁላችን በሁላችን ለሁላችን ሆኖ ተሰናስሎና ተሸምኖ የተበጀ የወል

ወይም የጋራ ማንነታችን መሆኑን ያስረዳል ፡፡በዚህም

ምክኒያት እኛም የኢትዮጵያ ማንነት የጋራ ማንነት መሆኑን በጽኑ እናምናለን፡፡ ከኢትዮጵያ ማህበረሰቦች አንዱ የሆነው የአማራ ህዝብ በሃገረ-መንግስቱ ምስረታና ግንባታ ሂደት ጉልህ አበርክቶ ያደረገ ታላቅ ህዝብ ነው፡፡ ይህ አበርክቶው ላለፉት 60 ዓመታት በጥላትነት አስፈርጆ ለተካሄደበት እና እየተካሄደበት

ላለው ስም ማጥፋት፣ውንጀላ፣ መሳደድ እና ዘር ማጥፋት አደጋ የዳረገው በለን እናምናለን፡፡

በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መባቻ ጀምሮ በአውሮፓ

እየተቀጣጠለ የመጣው ስር-ነቀል የማህበረሰባዊ የለውጥ ሂደት ማለትም ስርዓተ መንግስት፣ስርዓተ ትምህርት፣ስርዓተ ማህበር እኛ ስርዓተ ምርት ዘግይቶም ቢሆን ወደ ሀገራችን የገባው አሁን ሀገራችን ለምትገኝበት ምስቅልቅል ቀጥተና ምክኒያት መሆኑን እንረዳለን፡፡ከነገስታቱ መንግስታዊ ስርዓት

ጀምሮ የአውሮፓን ማህበረሰባዊ ለውጥ ሂደት ተሞክሮዎች ከሀገራችን ነባር ማህበረሰባዊ ለውጥ ተሞክሮዎች አንጻር ሳይመረምሩና ሳይፈትሹ ለመቅዳት መሞከራቸው ውሎ አድሮ ከሃገራችን ነባር ፍልስፍና ፣መርህና እሴት ጋር ግጭት በመፍጠሩ ሀገሪቱን ለህልውና አደጋ የዳረገ መሆኑን

እንገነዘባለን፡፡ በተለምዶ የ60ዎቹ ትውልድ በመባል የሚታዎቀው የትውልድ ክፍል የአውሮፓን የማህበረሰባዊ የለውጥ ሞዴል የመጀመሪያና የመጨረሻ ብቸኛ አማራጭ አድርጎ መውሰዱ

ብቻ ሳይሆን ነባሩን የኢትዮጵያ ማህበረሰባዊ የለውጥ ሞዴል በጨለማነትና በኋላ-ቀርነት በይኖ መነሳቱ አሁን ሀገሪቱ ለምትገኝበት የህልውና አደጋ የአንበሳው ድርሻ ይይዛል፡፡ ነጻነት፣እኩልነትንና የስልጣን ጥያቄን በማቀንቀን የተነሱት የ60ዎቹ ትውልዶች ጨቋኝና ተጨቋኝ ታሪክና ትርክት

በመፍጠር ለራሳቸውና ማህበራዊ መሰረታችን ነው ብለው ለሚያምኑት ማህበረሰብ ለስነ-ልቦና ስብራትና ለበታችነት ስሜት በመዳረግ ጨቁኖናል ብለው የሚያምኑትን የማህበረሰብ ክፍል ማህበራዊ እረፍት በመንሳት እና ዘሩን ለማሳት የሞከሩት ትግል ባለመሳካቱ ዘር ወደ ማጥፋት ደረጃ እንዲሸጋገሩ የዳረጋቸው፡፡ የአማራ ህዝብ ጥያቄ ሌሎች ማህበረሰቦች ያቀነቀኗቸው ጊዜያቸው ያለፈባቸው ተሞክረው የወደቁ ውጤታቸውም በአውዳሚነት የሚጠናቀቁ የነጻነትና የእኩልነት ጥያቄዎች

አይደሉም ፡፡የአማራ ህዝብ ከምንም ነጻ ለመሆን ከማንም እኩል ለመሆን አይታገልም ነጻነትና እኩልነት የዘመናት እሴት አድርጎ የያዛቸው ስልሆኑ፡፡

የአማራ ህዝብ ጥያቄ የአማራ ብልጽግና እንደሚለው

የአማራ ህዝብ ትግል ጅማሮ ላይ የተነሱ ከወሰንና ከማንነት፣ ከህገ-መንግስት መሻሻል፣በሃገሪቱ ተዘዋውሮ ከመስራትና ከመንቀሳቀስ ጋር የተያያዙ አስተዳደራዊ እና ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን ተሸገሮ፤ በተሳሳተ ፍልስፍና፣ታሪክና ትርክት ተመስርተው እየተፈራረቁ ለስርዓታዊ በደል፣ማህበራዊ እረፍት እና አሁን ለተጋረጠበት የዘር መጥፋት ወይም የህልውና አደጋ የዳረጉ መንግስታዊ ስርዓቶችንና የተመሰረቱበትን መተክላዊ ሃሳብ በመንቀል ሀገራዊ ፍልስፍና እና እሴትን ከዘመናዊ ፍልስፍናና እሴት ጋር ያሰናሰለ በሃቀኛ ታሪክና ትርክት ላይ የተመሰረተ መንግስታዊ ስርዓት ማንበርና በሃገራዊ አንድነት ላይ የተቃጣውን አደጋ በማስቀረት ሀገራዊ አንድነትን ማስጠበቅ ወደ መሆን ተሸጋግሯል፡፡ ፋኖነት ኢትዮጵያ የውስጥም የውጭም ጥላት በአንድነቷና በነጻነቷ ላይ አደጋ በተደቀነበት ወቅት የአደጋ ጊዜ ተጠሪና መውጫ ኃይል የሆነ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ማህበረሰቦች እሴት መሆኑን በጽኑ እናምናለን፡፡ለዚህም ታሪክና አሁን ላይ በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች እየቀረበ ያለው የትግል የአጋርነት ተሳትፎ ህያው ምስክሮች ናቸው፡፡ስለሆነም የአማራ ህዝብን ህልውናን እና የሀገሪቱን አንድነት እየተፈታተነ ያለውን ፈሪና አረመኔያዊ ስርዓት ከመሰረቱ ነቅሎ ለመጣል ከታች በተዘረዘሩት ምክኒያቶች የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ በመመስረት ትግሉ የሚጠይቀውን የአደረጃጀት የአመራርና የማስፈጸም ብቃት ማሳደግ አስፈልጓል፡፡

1. የትግሉ ግብ በማደጉ፡-የአማራ ህዝብ ጥያቄ ሲጀምር አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ የነበሩ ሲሆን ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ ለማስመለስ የሞከረ ቢሆንም ምላሽ ከማግኝት ይልቅ በተቃራኒው ዘር ማጥፋት ነበር የታወጀበት ስሆንም ጥያቄዎቹ መልስ ማግኘት የሚችሉት በስርዓት ለውጥ ደረጃ ወደ ሚደረግ ትግል በማደጉ፡፡

2. የትግሉ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ በማደጉ ፡-በበጥቂቶች የተጀመረዉ ትግል መላዉ አማራን ከማነቃነቅ አልፎ በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያገባቸዉን ሁሉንም ማህበረሰቦች ወደ ማሳተፍ በማደግ ትግሉ የአደጋ ጊዜ መዉጫ ትግል መሆኑን አዉቀዉ በተስፋ የሚጠብቁት በመሆኑ እና ይህንን የህዝብ ንቅናቄ መሸከም የሚችል አደረጀጄት፣ አመራርና የመፈፀም አቅም ማሳደግ አስገዳጅ ስለሆነ፡፡

3. ከፊታችን የሚጠብቀንን ሀገራዊ ሃላፊነት በሚገባ መወጣት ያስችለን ዘንድ ከወታደራዊ ኃይሉ በትይዩ የሲቪል አስተዳደሩን መሸከም የሚችል ኃይል ማዘጋጀት ምቹ ሁኔታ መፍጠር ስለሚያሰፈልግ፡፡

4. የትግሉን ጊዜ ማሳጠር በማስፈለጉ፡- ትግሉ በተራዘመ ቁጥር ይህ ኃላፊነት የማይሰማዉ ስርአት በሀገሪቱ አንድነት እና በማህበረሰቦች መካከል የሚፈጠረዉ አለመተማመን አደጋ ስለሚጨምር ይህን ለመቀነስ ይቻል ዘንድ በተደራጀና በተቀናጀ አካሄድ ትግሉን ማሳጠር አስፈላጊ በመሆኑ፡፡

5. የሌሎች ብሔሮች ወይም ነገዶች በትግሉ የመሳተፍ ፍላጎትና ጥያቄ እየጨመረ በመምጣቱ ለዚህም ምቹ ሁኔታን መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፡፡

6. ትግሉ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱ፡- ይህ መደራጃዉን ፍርሀት ያደረገ አዉዳሚ ስርአት በወሳኝ መልኩ ጦርነቱን ተሸንፏል ብለን እናምናለን፡፡ ለዚህም ተስፋ በቆረጠ ስሜት በምክርቤት ጭምር የሀገሪቱን ግዙፍ ተቋማትና ፕሮጀክቶች በመሸጥና በማቆም ለመዋጋት መወሰኑ እንደ ማስረጃ መውሰድ ይቻላል ፡፡ ይሁንና በወታራዊ አውደ ውጊያ ማሳካት ያልቻለዉን ህልም በሌሎች አዉደ ዉጊያዎች ለማካካስ ርብርብ እያደረገ ይገኛል፡፡ ለአብነት ፋኖን ከህዝቡ ለመነጠል ይረዳኛል ያለዉን አንደኛ ለመንግሰት ተጠሪ የሆነ ቀማኛና ዘራፊ ቡድን በፋኖ ስም በማደራጀት ሁለተኛ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ገንዘብ በመመደብ በትግሉ ዉስጥ የሚሳተፉ ግለሰቦችና ቡድኖችን በጥቅም በመደለል ሶስተኛ በድርድር ስም የስልጣን ፍላጎት ያላቸዉንና የትግሉ እድገት ጋር አብሮ ማደግ ያልቻሉትን ግለሰቦች በመሸንገል አራተኛ የህዝባችንን የመሰረተ ልማት አቅርቦት፣ የሸቀጥ ዝዉዉርን፣ የትምህርትና የጤና አገልግሎት አቅርቦትን፣ የግብርና ቴክኖሎጂ አቅርቦትን ወዘተ… በማስተጓጎል ህዝቡ እንዲማረርና ከትግሉ እንዲነጠል ለማደረግ የሞት ሽረት ርበርብ እያደረገ ይገኛል፡፡ ስለሆነም የትግሉን አደረጃት፣ አመራርና የመፈፀም አቅም በማሳደግ ሊፈጠር የሚችል የትግልክፍተትን በመሙላት ስርአቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ እስከ ወዳኛዉ ማስወገድ በማሰፈለጉ፡፡

7. አለማቀፉ ማህበረሰብ የትግሉን ምንነት፣ አስፈላጊነትና አደረጃጀት የበለጠ በሚረዳዉ ቅርፅና መልክ ማደራጀት አስፈላጊ ሆሞ በመገኘቱ እና በእነዚህና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች ዕዙ ሊመሰረት ግድ ሁኗል፡፡ስለሆነም እኛ በመላው የወሎ ምድር በተለያየ አደረጃጀት እና ቅርጽ የምንቀሳቀስ የፋኖ ሃይሎች ተገናኝተን ባደረግነው ታላቅ ጉባኤ ከትብብር ወደ አንድነት በመሳደግ ዕዙን የመሰረትን መሆኑን ለተከበረው የአማራ ህዝብ፣ ለኢትዮጵያውያን፣በመላው ዓለም ለምትገኙ የትግሉ ደጋፊዎችና የትግል አጋሮቻችን ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው፡፡

በዚህ መሰረት

📌1ኛ.የዕዙ ስያሜ የአማራ ፋኖ በወሎ ዕዝ

📌2ኛ.የዕዙ አደረጃትና ሃላፊነት

የዕዙ ዋና አዛዥ ፋኖ ኮ/ል ፈንታው ሙሃባው

📌የዕዙ ም/አዛዥ ፋኖ ምሬ ወዳጆ

📌የዕዙ አስተዳደር ፋኖ አለምነው መብራቱ

📌የዕዙ ሎጅሰቲክ አዛዥ ፋኖ ኮ/ል ሞገስ ዘገየ

👇የዕዙ የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ፋኖ ሻፊ ሃብታሙ ሆነው

በጉባኤው በአብላጫ ድምጽ መመረጣቸውን እየገለጽን

ትግሉ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱን በማስገንዘብ ከዚህ

በታች ለጠቀስናችሁ አካላት እንደሚከተለው ጥሪያችን

እናስተላልፍላችኋለን ፡፡

ለተከበረው የኢትዮጵያ ህዝብ፡-

ትግላችን ሁለንተናዊ የህልውና አደጋ የተጋረጠበትን የአማራ

ህዝብ መታደግና የሀገራችን አንድነት እና ሉዓላዊነት

ማስጠበቅ መሆኑን ተገንዝበሃል ብለን እናምናለን ፡፡ለዚህም

ለትግሉ ተሳትፎህንና አጋርነትህን በማሳየት

አረጋግጠሃል፡፡ስለሆነም በስሁት ፍልስፍና፣ታሪክና ትርክት

ተመስርቶ የጋራ ማንነታችን ለማጥፋትና ሀገራችንን

ለመበተን አበክሮ እየሰራ ያለውን ፈሪና ድንጉጥ መንግስታዊ

ስርዓት ከኢትዮጵ ጫንቃ ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ

አሽቀንጥሮ ለመጣል የምናደርገውን ትግል የበለጠ

ተሳትፎህንና አበርክቶህን እንድታጠናክር አጥብቀን

እንጠይቃለን፡፡

ለተከበረው የአማራ ህዝብ፡-

ሁሉን አቀፍ መንግስታዊ በድልንና አሻጥርን ተቋቁመህ

ስርዓቱን ለመንቀል የምናደርገውን ትግል

በልጆችህ፣በገንዘብህና በስነ-ልቦናህ እየከፍልህ ያለውን

መስዋዕትነት እንደ በፊቱ ሁሉ በታሪክ ፊት የምትከብርበትና

የምትኮራበት መሆኑ ጥርጥር የለውም ፡፡ስለሆነም ትግሉ

በአጭር ጊዜ ተቋጭቶ ማህበራዊ ዕረፍት ታገኝ ዘንድ

ለምናደርገው ትግል የተለመደውን ሁለንተናዊ ድጋፍና

ትብብር እንዳይለየን እንጠይቅሃለን፡፡

ውጭ ለምትኖሩ የትግሉ አጋርና ደጋፊዎቻችን፡-

ሙያችሁን ፣ገንዘባችሁንና ጊዜችሁን ሰውታችሁ

ያለመሰልቸት የምታደርጉት ተጋድሎ ሁሉ በሃገራችን

የለውጥ ታሪክ አይረሴና ጉልህ አሻራ መሆኑን በፍጹም

ልባችን እናምናለን፡፡ስለሆነም ትግሉ የበለጠ ቅርጽና መልክ

ኑሮት በቋፍ ላይ ያለችውን የጋራ ሀገራችን እንታደግ ዘንድ

በመካከላችሁ የሚስተዋሉ ጥቃቅን መጓተቶችን በመቅረፍ

የተለመደውን የትግል አጋርነታችሁን እንድታጠናክሩ ጥሪ

እናስተላልፋልን፡፡

በየክፍለ-ሀገሩ እየተዋደቃችሁ ላላችሁ የትግል ጓዶቻችን፡-

የትግሉ ወሳኝ ምዕራፍ መድረሱና ለህዝባችን እና ለሀገራችን

ትግሉን በአጭር ጊዜ የመጠናቀቅ አስፈላጊነት አጣዳፊና

ወቅታዊ መሆኑን ተገንዝበን ከትብብር ወደ አንድነትና

ውህደት ለመምጣት የምናደርገው ርብርብ የተሳለጠና

የተቃና እንዲሆን ፤ ጥላት ይህ አንድነት እውን እንዳይሆን

በመካከላችን እያደረገ ያለውን አሻጥር ወደ ጎን በመተው

ወደ አንድነትና ውህደት በፍጥነት እንድንመጣ በተሰው

ሰማዕታት ወንድሞቻችንና በአማራ ህዝብ ስም ወንድማዊ

ጥሪያችን እናስተላልፋልን፡፡

ለመከላከያ ሰራዊት፡-

ከሀገር ደጀንነትና ጠባቂነት ክብርህ ወደ ቡድንና ግለሰብ

ስልጣን ጠቢቂነት አዋርዶ ፤ንቃትህንና ህሊናዊ ሁኔታህን

በማራከስ፤መስመራዊ መኮንኖችህንና የበላይ አመራሮችህን

በጥቅም በመደልል ፤ዓላማ በሌለውና የኩራትህ ምንጭ

ከሆነው ህዝብህ ጋር ደምህን እንድታፈስና አጥንትህን

እንድትከሰክስ ፣ተዋርደህ እንድትበተን በማድረግ ስርዓቱ

ሀገር አፍርሶ ሀገር ለማዋለድ ለያዘው ፕሮጀክት

ማስፈጸሚያ እያደረገህ መሆኑን ተገንዝበህ ሀጊሪቱን ከብተና

ለመታደግ የምናደርገውን ትግል እንድታግዝ ሀገራዊ ጥሪ

እናቀርብልሃለን፡፡

ለአማራ ብልጽግና ፡-

የአማራ ህዝብ ጥያቄ አንተ እንደምትለው የማንነትና

የወሰን፣የህገ-መንግስት መሻሻልና መፈናቀልና መሰደድ እንዲቆም የሚል አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች የተሸገረ እና ጥያቄዎቹ መልስ የሚያገኙት መንግስታ ስርዓቱና ስርዓቱ የተመሰረተበትን አስተሳሰብ ከስሩ መንቀል ወደ ሚል ተሸጋግሯል፡፡ስለሆነም ሳይመሽብህ የተላላኪነትና የባንዳነት አመልህን ጥለህ አይቀሬውንና አሸናፊውን የአማራ ህዝብ ትግል ከማጓተትና ከማደናቀፍ እንድትታቀብ በድጋሜ እናስጠነቅቅሃለን፡፡ ‹‹እየመጣን ነው››

የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ

ማሳሰቢያ

በእዚህ የዕዝ አደረጃጀት ውስጥ ለመደራጀት የምትፈልጉ ነባርም ሆናችሁ አዲስ የምትመሰረቱ የትግል ሃይሎች በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ መቀላቀል የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

R:0 / I:0 / P:1 [R] [G] [-]

ከጎጃም ዕዝ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ!

እንደሚታወቀው የአማራ ህዝብ በፋሽስታዊው አገዛዝ ሁሉን አቀፍ ጭፍጨፋ (ዘር ማጥፋት) እየተካሄደበት ይገኛል። የህልውና አደጋ የተደቀነበት የአማራ ህዝብ ተፈጥሯዊ የሆነውን እራስን መከላከል እና የመኖር መብቱን ለማስከበር ተደረጅቶ የአገዛዙን አከርካሪ በመስበር ትግሉን እያቀጣጠለውና አላማውን ለማሳካት በመገስገስ ላይ ይገኛል።

የጎጃም ዕዝ ከምስረታው ጀምሮ እስካሁን እያደረገ ባለው እንቅስቃሴ አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግቧል፤ እያስመዘገበም ይገኛል። የጎጃም ፋኖ ከአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት እየማረከ ከነፍስ ወከፍ እስከ ቡድን መሳሪያ ድረስ ታጥቋል። የክላሽንኮቭ እጥረት የነበረበት ፋኖ አሁን ላይ የስናይፐር፣ የመትረየስ፣ የድሽቃ ፣ ሞርታር፣ እና ዙ-23 ባለቤት ሆኗል።

ይህ የሆነው ደግሞ የዘወትር የሎጅስቲክ አቅራቢያችን ከሆነው የአገዛዙ ጨፍጫፊ ሃይል መሆኑ ታውቆ ያደረ ሀቅ ነው። አማራ እንዲጠፋ የታቀደበት፣ በድኑ እንኳ እንዲሰደድ የተሴረበት ህዝብ በመሆኑ ለትግሉ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በቁርጠኝነት ተነስቷል።

የፋሽስት አገዛዙ በአማራው አንገት ላይ ያስገባውን የወፍጮ ድንጋይ በአማራ ብርቅየ የቁርጥ ቀን ልጆቹ ብርቱ ትግል እያወላለቀ ይገኛል። “በፍርድ ከሄደችው በቅሎየ ያለፍርድ የሄደችው ጭብጦየ” እንዲል ብሂሉ፤ የአማራ ህዝብ ለርትዕና ፍትህ የሚታገል፤ የመለኮትን አኗኗር የሚተረጉም፤ የጥበብ ባህርና የትንቢት ጥልቀት የተነተነ፤ እይታው በንስር አምሳል የተሰየመ፤ ቤት ከመስራት በላይ ሀገረ መንግስት መገንባት የሚቀለው ህዝብ ነው።

ከልቡ ለሚወደው ህዝብ ነፍሱ ጠርታው እናትና አባቱን፣ ልጅንና ሚስቱን ትቶ እንደ መክሊቱ ወደ ትግል ያልገባ ፋኖ የለም። ለአማራ ህዝብ ነፃነት ነፍሱን አስይዞ በሂወት የመኖር መብቱን በክንዱ ለማስከበር ውቅያኖስ የማይሰነጥቅ፣ በረሃ የማያቋርጥ፣ ተራራ የማይቧጥጥ ፋኖ የለም።

ንስሃውን ከሚሰማው፣ ምህላውንና ዱዓውን ከሚቀበለው አምላክ ፊት እንደሚቀርብ የዕጣን መስዋዕት የአማራ ህዝብ ጭፍጨፋ ልቡን የማያነደው የአማራ ፋኖ የለም። በአሁኑ ሰዓት እንዲጠፋ ለተፈረደበትና ለህልውና ለሚታገለው የአማራ ህዝብ ትግል ጎን መቆምና ለአማራ ህዝብ መታገል በሃይማኖት እንደ ቅድስናም እንደ ምሁርነትም የሞራል ልዕልናም ተደርጎ ይቆጠራል ብለን እናምናለን።

ትግሉ የህልውና ትግል በመሆኑ የአሁኑ የአማራ ህዝብ ትግል መሳሳትን የሚፈቅድ አይደለም። ዕዙ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከተወያዬ በኋላ ባለ 4 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

1ኛ. በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ሲስተዋል የነበረው ከፋሽስት አገዛዙ ጋር “የድርድርም ሆነ “የንግግር ‘ የሚመስሉ ሀሳብና አስተያየቶች በበርካታ የዕዙ አባላትና ደጋፊዋች እንዲሁም ማህበረሰባችን ዘንድ ብዥታን ስለፈጠረ “የድርድር ወይም የንግግር” ጉዳዩ ዕዙን የማይመለከት መሆኑን በግልፅ ማሳወቅ እንፈልልጋለን።

የአማራ ህዝብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ፃታ ሳይመርጥ ለህልውና ትግሉ ነፍጥ አንግቦ እየተዋጋ ይገኛል። በዚህ የህልውና የትግል ወቅት አገዛዙ ባሰማራው ሰራዊት በከባድ መሳሪያ ህፃናትና አዛውንቶች ተጨፍጭፈዋል፤ መስጊድና ቤተክርስትያን ተቃጥለዋል። የህዝባችን ንብረት ወድሟል ተዘርፏል። እንዲሁም አሰቃቂ ድርጊቶች በህዝባችን ላይ ተፈጽሟል።

እንደ ጎጃም ዕዝ የአማራ ህዝብ ማሸነፍ ብቻ ነው ምርጫው ብለን እናምናለን። ነገር ግን የፋሽስት አገዛዙ መሸነፉን አረጋግጦ ድርድር የሚፈልግ ከሆነም እንኳ የትግሉ ባለቤት ከሆነው ከመላው የአማራ ህዝብ (ጎጃም፣ ጎንደር፣ ወሎ፣ ሸዋና ከክልሉ* ውጭ ካለው ህዝባችን) እንዲሁም ከትግል አጋር ኢትዮጵያውያን ጋር ተመካክረን በግልፅ የምናሳውቀው እንጂ የጓዳ ቤት ድርድር የማይኖር ብቻ ሳይሆን የማይታሰብ መሆኑን በአፅኖት እየገለጽን ትግሉ እንደ ጎጃም ሳይሆን እንደ አማራ መሆኑን ሁሉም እንዲረዳው እንፈልጋለን።

2ኛ. ቤተ እምነቶቻችንን ከሚያረክስ፣ ቤተክርስትያንን ከሚያቃጥል፣ መስጊዶቻችንን ከሚያወድም፤ ቄሶችን፣ ሸኮችን፣ ድያቆንና ደረሳዋችን፤ ህፃናትና እናቶችን ከሚደፍር፣ አዛውንቶችን ከሚያርድ የጠላት ሃይል ጋር የተሰለፋችሁ የፀጥታም ሆነ የፖለቲካ አመራሮች ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ ማሳወቃችን ይታወቃል። ይህን ማስጠንቀቂያ ተላልፋችሁ በተገኛችሁት የአማራ ጡት ነካሾችና የእፍኝት ልጆች ላይ ማንኛውንም የማያዳግም እርምጃ ከዛሬ ጀምሮ እየወሰድን እና በቀጣይነትም የምንወስድ መሆኑን ሊታወቅ ይገባል።

3ኛ. ለተለያዩ አካባቢዎች ምሳሌ የሆነውን “የጎጃም እዝ ፋኖ” ለማፍረስ እና የራስን ሃይል ለማደራጀት በአማራ ህዝባዊ ሃይልም ሆነ በአማራ ህዝባዊ ግንባር ስም የምትንቀሳቀሱ ግለሰቦች ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እያሳሰብን ለትግሉ ፈር ቀዳጅ ስለነበራችሁና ለከፈላችሁት ዋጋ ስለምናከብራችሁ በባለፈው መግለጫችን ለምንጠይቃችሁ ጥያቄ ምላሽ እንድትሰጡን እና በአሰላለፋ አንድ ሆናችሁ በእዙ መዋቅር በመግባት እንድታታግሉን ስንል ጥሪ ማድረጋችን ይታወቃል።

ነገር ግን ጥሪዎችን ተቀብሎ የተደረጉ ውይይቶች ደካማ መሆናቸውና እንደተቋም በቂ ውይይት ባለመደረጉ ለመጨረሻ ጊዜ በቅርብ ቀን ጥሪያችንን አክብራችሁ ተገኝታችሁ ጥያቄዎቻችንን እንድትመልሱልን እያሳሰብን ይህን ማድረግ ካልቻላችሁ በጎጃም እዝ የትእዛዝ ሰንሰለት ውስጥ ማንኛውም አካል እንደልቡ ልዩነቶችን እያሰፋ አደረጃጀት መያዝም ሆነ መንቀሳቀስ የማይቻል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።

4ኛ. ተሽከርካሪዎችን በተመለከተ የመኪኖችን እንቅስቃሴ በመጠቀም የጨፍጫፊው ሃይል ደህንነቶችንና ኦፒዎችን እያሰማራ በድሮንና በሜካናይዝድ ከሞርተር እስከ ቢኤም በከባድ መሳሪያ ንጹሃንን እየጨፈጨፈ ይገኛል።

በተጨማሪም በሚዲያ ቀርቦ በአደባባይ ሸቀጣሸቀጦች ስንዴን ጨምሮ መድሃኒቶች ወደ አማራ “ክልል” እንዳይገባ ትእዛዝ ተሰጥቷል። በተቃራኒው ከከሰል እስከ ማርና ቂቤ፣ ከስንዴ እስከ ጤፍ ድረስ ከፍተኛ በጀት ተመድቦ እየገዛ ሲሆን አላማውም ጦርነትን በማራዘም የአማራን ህዝብ በርሃብ አለንጋ እንዲገረፍና በኢኮኖሚው እንዲዳከም በመዋቅራዊ መንገድ ታቅዶበት እየተሰራ መሆኑ ታውቋል።

ስለሆነም የፋሽስቱ ዙፋን ጠባቂ የሆነው ሀይል ከክልሉ እስኪወጣ ድረስ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንደማይደረግ በአፅኖት መግለፅ እንፈልጋለን።

የተሽከርካሪ ባለንብረቶች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የዚህ እኩይ ተግባር ተሳታፊ ሆናችሁ እንዳትገኙ እያሳሰብን ይህን መመሪያ ተላልፎ በተገኘ ተሽከርካሪ ላይ ለሚወሰደው እርምጃ ሃላፊነቱን እራሱ አሽከርካሪው ወይም የተሽከርካሪው ባለቤት ይወስዳል።

ከእውነት ጋር የቆመ ህዝብ ያሸንፋል!!

ድል ለተገፋው የአማራ ህዝብ!!

ድል ለፋኖ!!

የጎጃም ዕዝ ፋኖ!

ታህሳስ 02/2016 ዓ.ም

R:0 / I:0 / P:1 [R] [G] [-]

ከምስራቅ አማራ ፋኖ የተላለፈ ጥሪ

ዘመቻ_ጃውሳ

ዛሬ ህዳር 20/2016 ጧት ጀምሮ ምስራቅ አማራ ፋኖ ዘመቻ ጃውሳ በማለት የሰየመዉን የሞትሽረት ትግል መላዉ አማራ ታጋይ ተቀላቅሎ ለአንደየ እና ለመጨረሻ ጊዜ የወራሪዉን ሀይል በገባበት ቦታ ሁሉ ድባቅ እየመታ ትጥቁን እንዲቀበለዉ ሲል ለሁሉም አማራ ህዝብ ጥሪ አስተላልፏል ።

ዘመቻ ጃውሳ ባለዉ ህዳር 20 በጧት በጀመረዉ ኦፕሬሽን ምስራቅ አማራ ፋኖ በሰሜን ምስራቅ በኩል የተሰለፈው የራያ ብርጌድ የዞብልና የራማ ተራራን ከባዱን ምሽግ ሰባብሮ ቀዩ ጋራ፥መደራራና ጮሬን ተቆጣጥሯል። ከዞብልና ከራማ ተራራዎች የተረፈዉ ወራሪ ሃይል

ለመዉጣት ቢሞክርም በምስራቅ አማራ ፋኖ #ካላኮርማ

ብርጌድ ዋናዉን የቆቦ አስፓልት ይዘው ሮቢት ላይ ቆርጠዉ ድባቅ እየመቱት ይገኛሉ።

ወደ ደጋማዉ ክፍል አቦሆይ ጋራን መጠጊያ ለማድረግ ከጮቢ ላስታ መነሻዉን አድርጎ ለማምለጥ የሞከረው ነበልባሎቹ ምስራቅ አማራ ፋኖ ዞብል አንባ ብርጌድ ጨፌ መደር ላይ ድባቅ እየመቱት ይገኛሉ። ከግዳንና ከአካባቢዉ ሰባስቦ ወደራያ በደጋማዉ ክፍል በፋኖ እየተገረፈ ያለዉን ወራሪ ሃይል ለማገዝ በወዳች በኩል ለመግባት የሞከረዉ ወራሪ ሃይል #በምስራቅ አማራ ፋኖ የጦር ማሃዲሶቹ የጃኖ አበበ ልጆች #ሃዉጃኖ ብርጌድ ደጋው ክፍል ላይ ድባቅ እየመቱት ይገኛሉ። ከደቡብ ወሎ የሰሜን ወሎዉን ወራሪ ሃይል ለመታደግ እሚሞክር ሃይል ካለ ለጊዜዉ መግለጽ ባልተፈለገበት ቦታ የምስራቅ አማራ ፋኖ አሳምነዉ ብርጌዶች በምድር ድሮኑ መሪነት እየተመሩ እየተጠባበቁት ይገኛሉ ። አሁን ላይ ጥላት በዋርካዉ ምሬ ወዳጆ የተመራዉን ዘመቻ ጃውሳ እሚለዉን ኦፕሬሽን መቋቋም አቅቶት እየሽሸ በመሆኑ መላዉ አማራ ወራሪ ሃይሉን መንገድም እዳታሳይ ልብስም እዳትቀይርለት የጥላትህን ትጥቅ ማርከህ ታጠቅ ሲል ከምስራቅ አማራ ፋኖ ጥሪ አስተላልፏል።

R:0 / I:0 / P:1 [R] [G] [-]

ከልጅ እያሱ ክፍለ ጦር የተሰጠ መግለጫ

የገጠመንን የህልውና ትግል ቀልብሰን ህዝባችን ለመታደግ ነፃነታችንን በክንዳችን ለማረጋገጥ ታሪካችን በእጆቻችን ለመፃፍ አንድ ሆነን ከመታገል ውጭ ሌላ አማራጭ አለመኖሩን አውቀን አንድነታችን አጠንክረን ጠላቶቻችን እንዳሰቡት ሳይሆን በተቃራኒው ድልን እየተቀናጀን እንገኛለን።ስለሆነም አጠቃላይ በደቡብ ወሎ ዞን ወረዳ ውስጥ የሚገኙ የፋኖ አደረጃጀቶች በብርጌድ ተደራጅተው ወደ አንድ ክፍለ ጦር በመምጣት የልጅ እያሱ ክፍለ ጦር በሚል ተቋቁሟል።

በዚህ መሰረት የልጅ እያሱ ክፍለ ጦር የጋራ ስራ አስፈፃሚ በማዋቀር ሰባት ብርጌዶችን በመያዝ መመስርት ችሏል። የብርጌዶቹ ስምና የሚቀሳቀሱበት ቦታ እንድሁም አዛዥና ምክትል አዛዥ እንደሚከተለው ተቀምጠዋል።

1.ንጉስ ሚካኤል ብርጌድ

ዋና አዛዥ ፋኖ ሰለሞን አሊ

ምክትል አዛዥ ፋኖ አብይ ከበደ

የሚንቀሳቀስበት ቀጠናና

1.ደሴ ከተማ

2.ደሴ ዙሪያ ወረዳ

3 አልብኮ ወረዳ

4 ኩታበር ወረዳ

5.ኮምቦልቻ

2.አሳምነው ብረጌድ

መሪ ፋኖ ዶክተር ሙሉጌታ ድጋፌ

ምአዛዥ ሙሉጌታ የሺጥላ

የሚቀሳቀስበት ቀጠባ

1.አማራ ሳይንት ወረዳ

2.ሌጋምቦ ወረዳ

3.ቦረና ሳይንት ብሄራዊ ፓርክ

3.መቅደላ ብረጌድ

ዋና አዛዥ 50 አለቃ ሰይድ ሙሀመድ

ም/አዛዥ 10 አለቃ ጌትነት ታደሰ

የሚሽፍኑት ቀጠና

1. ማሻ ወረዳ

2. ተንታ ወረዳ

3.ቱላአውሊያ /ጊምባ

4.ሚንሊክ ብርጌድ

ዋና አዝዥ ፋኖ አብነው ታደሰ

ምክትል አዛዥ መቶ አለቃ በላይ መከተ

የሚንቀሳቀስበት ቀጠና

1.መካነሰላም (ቦረና) ወረዳ

2.ወግድ ወረዳ

3.ከለላ ወረዳ

5.ታዘበው ብረጌድ

ዋና አዛዥ ኑረድን

ምክትል አዛዥ ወልደ ታደሰ

የሚቀሳቀስበት ቀጠና

1,ጃማ ወረዳ

2,ወረኢሉ ወረዳ

3.ደገር

4.ለገሂዳ ወረዳ

6.ቴዎድሮስ ብርጌድ

ዋና አዛዥ ፋኖ አባተ ካሳነህ

ም/አዛዥ 100 አለቃ ተገኔ አለባቸው

የሚቀሳቀስበት ቀጠና

1.ኮምቦልቻ ከተማ

2.ተሁለደሬ ወረዳ (ሀይቅ)

3.ቃሉ ወረዳ

4 አምባሰል ወረዳ

5.ደላንታ ወረዳ

7.አትሮንስ ብርጌድ

ዋና አዛዥ ይታገስ አራጋው

ምክትል አዛዥ ሻምበል ጀምበሩ

የሚቀሳቀሳበት ቀጠና

1.መሀል ሳይንት ወረዳ

2.ቦረና ሳይንት ብሄራዊ ፓርክ

3.ሌጋምቦ ወረዳ በዚህ አደረጃጀት ውስጥ የአማራን ህዝብ ህልውና ለማስከበር እና የመጣብንን ፈተና ለመቀልበስ እንድሁም አብሮን ለመታገል የሚፈልግ አካል በብርጌድ፣ በሻለቃና በሻምበል እየተዋቀረ ለሚመጡ እና አብሮን ለስራት ፋላጎት ያለው ሁሉ አብረን ለመስራት በራችን ክፍት መሆኑንና በክፍለ ጦሩ ስር ለመካተት ፍቃደኝነታችን ከወደሁ ለማሳወቅ እንወዳለን።

ድል ለአማራ ህዝብ

ዘላለማዊ ክብር ለትግሉ ሰማእታት‼

R:0 / I:0 / P:1 [R] [G] [-]

ከጎጃም ዕዝ የተላለፈ ጥብቅ መልዕክት

ሀገር መስራቹ: ሰው ወዳዱና ኩሩ ህዝባችን ሆይ:- በመጀመሪያው የጎጃም የክተት ዘመቻ በተለያዩ አውደ ውጊያዋች አመርቂ ድል አስመዝግበናል። ከአስተማማኝ ደጀን ህዝባችን ጋር በመሆን በርካታ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሳሪያዋችን ከጠላት ተቀብለን ታሪክ በወርቃማ ፈርጁ የሚያሰፍረውን ድንቅ ስራ ሰርተናል። እየሰራንም እንገኛለን። ህዝባችን ያመረተውን አዝዕርት በሚሰበስብበት በዚህ ወቅት አውዳሚውና የፋሽስት አገዛዙ ሰብሉን እንደ ጧፍ እያነደደ ወጣቱንም ሆነ ህፃንና አዛውንቱን በሞርታር በድሽቃና በድሮን እየጨፈጨፈን ይገኛል። የአርሶ አደሩ ሰብል መድረሱን ጠብቆ ሀገር መጋቢ የሆነው ህዝባችን ያመረተውን እህል በሞርታር እያቃጠለ ይገኛል። አመት ሙሉ የለፉበት ሰብል የተቃጠለባቸው አርሶ አደሮች ራሳቸውን አጥፍተዋል። ጠላት ገብቶ ባወደመባቸው አካባቢዎች ህፃናትና አሮጊቶች ተገለዋል። ሴቶች ተደፍረዋል። ቤቶች ተቃጥለዋል። ይህ ፋሽስታዊ አገዛዝ አላማው አማራውን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት መሆኑ ታውቆ ያደረ ሀቅ ነው። ይህ ጨፍጫፊና አውዳሚ አገዛዝ መንገድ መሪ ባንዳዋችን እና ምስለኔዋችን በመጠቀም አሁንም መዋቅራዊ ጭፍጨፋ ለመፈፀም እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ሀገር መስራቹ: ሰው ወዳዱና ኩሩ ህዝባችን ሆይ

እንዲታወቅልን የምንፈልገው :-

1.ይህ አውዳሚና ጨፍጫፊ አገዛዝ ህዝባችንን በረሀብ ለመቅጣት ሰብል እያቃጠለ ስለሆነ ስትለፉበት የከረማችሁበትን ከቃጠሎ የተረፈውን በአስቸኳይ እንድትሰበስቡ በአክብሮት እንጠይቃለን።

2.ወዶም ሆነ "ተገድጄ " ነው በሚል ሚዛን በሌለው ምክንያት ከጠላት ጋር እየተንቀሳቀሰ ያለ የትኛውም ግለሰብ ወይም ቡድን በማንኛውም ደረጃ ላይ ያለ ይሁን በታሪክም ሆነ አሁን ባለው ነባራዊ እውነት በጥቁር መዝገብ ተፅፎ የሚቀመጥና ዕዙም የማይታገስ መሆኑን ሊታወቅ ይገባል።

3. የሀይማኖት አባቶች ለምድ ለባሽ ተኩላ ሆነው በህዝባችን ላይ እየደረሰበት ያለውን ሁለንተናዊ ጭፍጨፋና ጥቃት የሚክዱ ሳይሆኑ የአቡነ ጴጥሮስን ፈለግ እንድትከተሉ በአክብሮት እየጠየቅን የለምድ ልብስ ለብሰው በሀይማኖት አባት ስም በህዝባችን የሚነግዱትን የማንታገስ መሆኑን በጥብቅ ሊታወቅ ይገባል።

4. ይህ አውዳሚ አገዛዝ ራሱ ሲያወድመው በከረመው ቢሮ ሲቪል ሰርቫንቱን ግቡ እያለ እያንገላታ እና ስልጣን አንፈልግም የሚሉ አመራሮችን የቁም እስረኛ እያደረገ ለስልጣን እያስገደደ መሆኑን አረጋግጠናል። ሆኖም ግን ትግሉ የመኖርና ያለመኖር በመሆኑ አርበኝነት እስከ መጨረሻው ህቅታ ለእውነት መቆም እንጂ በዲናር የሚቀየር ባለመሆኑ ጠላት በሚሰፍርላችሁ ረጥባ ሳትታለሉ በአቋማችሁ ፀንታችሁ እንድትታገሉና በዚህ ትግላችሁ ዕዙም ከጎናችሁ መሆኑን ለማሳወቅ እንፈልጋለን።

5. ይህን አውዳሚና ጨፍጫፊ አገዛዝ ፍትህ እኩልነትና ዴሞክራሲ ናፋቂ ኢትዮጵያን በተለይም ለህልውና የሚታገለው የአማራ ህዝብ በሙሉ ተሳታፊ መሆኑ ታውቆ ያደረ ሀቅ ነው። ትግሉም ግማሽ ጥቁር ግማሽ ፍቅር እንዳይሆን የፋሽዝም አገዛዙ ሰራዊት ከአማራ "ክልል" እስካልወጣ ድረስ ተሽከርካሪዎች ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ በዕዙ የተወሰነው እንደተጠበቀ ሆኖ በልዩ ሁኔታ ዕዙ ባሰባሰበው መረጃ መሰረት በድንገት በመንገድ የቆሙ መኪኖች መኖራቸውን: ወደ ቤተሰቦቻቸው እየሄዱ በመንገድ የተጉላሉ ዜጎች እንዳሉና ሌሎች ቅሬታዋችንም ከግምት ውስጥ በማስገባት ከህዳር 21/ 2016ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 23 2016ዓ.ም ድረስ ለተሽከርካሪዋች የተፈቀደ ስለሆነ በመንገድ የቆማችሁና የተጉላላችሁ እንዲሁም ለማህበራዊ ጉዳይ የምትንቀሳቀሱ በተገለፀው ቀነ ገደብ ብቻ እንድትጨርሱ እያሳወቅን ከተጠቀሰው ዕለት በኋላ ግን አሽከርካሪዎችም ሆናችሁ የአሽከርካሪ ባለቤቶች ከአምቡላንስ: ከባጃጅና ሞተር በስተቀር ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳታደርጉ በድጋሜ በጥብቅ እናሳስባለን ። ይህን ተላልፎ የተገኘ ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ውሎ ሙሉ ንብረቱ ለፋኖ ገቢ እንዲሆንና እንዲወረስ ተወስኗል። ኬላ በሚጥሱት ላይ ደግሞ ሀላፊነቱን አሽከርካሪዎች ወይም የአሽከርካሪ ባለቤቶች ይወስዳሉ። ይህንንም ህግ አክባሪው እና ታላቁ ህዝባችን ያውቀው ዘንድ

5.1. መኪናዎች ሲንቀሳቀሱ ፋሽስታዊው አገዛዝ ግዳጅ በማለት የአማራን ህዝብ ኢኮኖሚ ማዳከምና የራሱን ሎጅስቲክ ከቦታ ቦታ በማንቀሳቀስ ህዝባችንን መጨፍጨፍና ያመረተውን እህል ማቃጠሉን አጠናክሮ

በመቀጠሉ

5.2.ይህ ፋሽስታዊ አገዛዝ በጎጃም ውስጥ ብቻ ከ600 በላይ የደህንነት ሰዋችን እና ገዳዮችን ስላሰማራ ለህዝባችን ደህንነት ሲባል የትራንስፖርት አገልግሎቶች እንዲቆም ዕዙ ወስኗል።

5.3. ቀድመው የገቡ የፋሽስታዊ አገዛዙ ገዳይ የደህንነት አካላትን ከቦታ ቦታ እንቅስቃሴ ሳይኖር እርምጃ ለመውሰድና እንዲሁም ለጊዜው በማይጠቀሱ ምክንያቶች መሆኑን ሊታወቅ ይገባል ።

6. ፋሽስታዊ አገዛዙ እያደረሰ ያለው ሁለንተናዊ ጭፍጨፋ ስለሆነ የጎጃም ዕዝ አገዛዙን ከስሩ ነቅሎ ለመጣል ሁለተኛውን የክተት ዘመቻ ለማወጅ በዝግጅት ላይ ስለሆነ ለዚህም ሁሉም ህዝብ እንዲዘጋጅ እየጠየቅን አገዛዙን ማሽመድመድ የሚችሉ ማንኛውንም እርምጃዋች ለመውሰድ ዕዙ የተገደደ በመሆኑ ፍትህና ፍርድ አዋቂው ህዝባችን ይህንን አውቆ ዕዙ በሚሰጠው አቅጣጫ ብቻ እንዲመራ በጥብቅ እናሳስባለን ።

7. ሀገር መስራች : ፍርድ አዋቂና ሰው አክባሪው ማህበረሰባችን ሆይ:- ፋሽስታዊው አገዛዝ የተቀደሰውን ሊያረክስ: የለማውን ሊያወድም: ንብረትህን ሊዘርፍ ማንነትህን ሊገፍ የመጣ በመሆኑ ባገኘኸው አጋጣሚ ሁሉ ከጠላት ማርከህ ታጠቅ። የማረከው የጠላት ንብረት በሙሉ የራስህ ሆኖ ይመዘገባል።

ለአማራ ምሁራን የቀረበ ጥሪ:-

ምሁራዊ ድካም የመጨረሻ ግቡ እውነትን ለሕዝብ ማሳወቅ ነው። ችግሮችንና መፍትሄውን መጠቆም ነው። ከዚህ በቀር ምሁርነት የለም። ከዚህ ሌላ ያለ ምሁርነት አድርባይነት ነው። በልቶ፣ ጠጥቶ፣ ብቻ ለሆድ መኖር እና ለሕዝብ ያወቁትን ሳያሳውቁ መሞት ክህደትም ነው። ምሁርነት ደግሞ ክህደትን ይፀየፋል። መንግስታዊ የዘር ማጥፋት እየተፈፀመበት የሚገኘውን የአማራ ህዝብ ሁሉም አገር ወዳድ ምሁራን ህዝቡ እያደረገ ላለው የህልውና ትግል የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉና እንዲረባረቡ ጥሪ እናቀርባለን። አገዛዙ ገደብ በሌለው ሥልጣን፣ ገደብ በሌለው መልክ

ሕዝባችንን እየገደለ ይገኛል። ላለፉት 30+ አመታት

ለተጨፈጨፈው የአማራ ህዝብ የተጠየቀ ስለሌለ አሁንም መንግስታዊ ጭፍጨፋውን ቀጥሎበት ይገኛል። ጠያቂየሌለበት ሥልጣን ሕዝብን ካልገደለ አይረካም። መፍትሔው የአማራን ህዝብ የህልውና ጥያቄ መልሶ: እኩልነት: ፍትህ እና ዲሞክራሲ ነው። ሕዝብ ወደ ዲሞክራሲ የሚሻገረው በአንድ ኃይል የተነጠቀውን ነፃነቱን ሲያስመልስ ነው። ነፃነታችንን ለማስመለስ ሥልጣን ከጨበጠው ገዳይ መንግሥት ጋር መጋደል የተቀደሰ ትግል ነው።

በአማራ ስም ለተቀመጣችሁ አመራሮችና የፀጥታ አካላት :-

እናንተ ከአማራ አብራክ የወጣችሁ:ሆዳችሁ አምላካችሁ የሆነ: በአማራ ህዝብ እጅ የበላችሁ በአማራ ህዝብ እጅ የጠጣችሁ :በጨለማ ውስጥ የምትዳክሩ ወደ ሰቆቃ የምትጣደፉ: ሐሰትን የምትሰብኩ:የኦሮሙማ ምንጣፍ ጎታቾች ሆይ እስከመቼ በዚህ አይነት ጭፍንነት ውስጥ ትኖራላችሁ? ከአማራ ትግል ጎን በአንድነት ለነፃነት ለመቆም ሲቻላችሁስ የአማራን ምሉዕ የነፃነት መንገድ በማደናቀፍ እስከመቼ የትግል መንገዱን ለማራዘም ትሞክራላችሁ ? የተንጣለለው የአማራ ህዝብ ክቡር እሴት: የተፈጥሮ ውበትና ርትዕትነት ሀር ሆኖ ሳለላችሁ ስለምንስ አንቆ የሚይዛችሁን የኦሮሙማውን ጠባብ መናኛ መጎናፀፊያን ትመርጣላችሁ? የአመራርነት የጥበብ ቀንዲል ብርሀኑ ደብዝዞ ጭልጭል እያለ የነበረው ላለፉት 30 አመታት አሁን ላይ ግን ድፍን ጨለማ ውስጥ በገባበት በዚህ ወቅት ችግሩን በፈጠረው አስተሳሰብ፣ ችግርን መፍታት ስለማይቻል ከትግል አጋር ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን አዲስ አስተሳሰብ

የሚቀጣጠልበት ጊዜው አሁን ስለሆነ ከድንቁርናው ዓለም ቀማኞች ብትለዩ የሰላም ሀብታችሁ በእጃችሁ ይሆናል።

በመጨረሻም:-

የነፃነት ቀላል መንገድ የለውምና እልፍ የአማራ አናብስቶች ለነፃነት የተራራ ጫፍ ላይ ለመድረስ በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ማለፍ የትግሉ ባህሪ በመሆኑ እያለፉበት ይገኛሉ። የኦሮሙማው የፋሽዝም አገዛዝ በጎጃም አማራ ብቻ ከ20 ጊዜ በላይ የድሮን ጥቃት ፈፅሟል። በተለይም ሰሞኑን በሞጣ: በዋበር : በጎንጅ ቆለላ ባደረገው የድሮን ጥቃት ንፁሀንን ጨፍጭፏል። እንስሳትን ገድሏል። የእዙ አመራርና

ሎጅስቲክ ክፍል ከሆኑት ፋኖ አርበኛ ተፈራ ጀምሮ ጀግና ጓዶችንም አጥተናል። በዚህም የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ጀግኖቻችንን የሚመጥን የተግባር ስራ ሰርተን እናሳያለን። ይህ የአማራ ትግል የመኖርና ያለመኖር በመሆኑ ምርጫችንም ማሸነፍ ብቻ ስለሆነ አሸናፊነት ደግሞ ውርሳችን ስለሆነ ፈተናዋችን ተቋቁመን በድል እንወጣዋለን። ፋኖነት ከአባቶቻችን የወረስነው ትጥቅና ስንቃችን ስለሆነ

ይህን ፋሽስት አገዛዝ ተፋልመን ከአካባቢያችንም ሆነ

ከሀገራችን ነቅለን እኩልነት ፍትህ እና ዴሞክራሲን

እናሰፍናለን።

ህዝብ ያሸንፋል!

ድል ለአማራ ፋኖ!

R:0 / I:0 / P:1 [R] [G] [-]

ከጎጃም ዕዝ ዘመቻ መምሪያ የተላለፈ አስቸኳይ መልዕክት

የፋሽስቱ የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ በአማራ ሕዝብ ላይ ሙሉ ጦርነት በማወጅ በከባድ መሣሪያና በድሮን የታገዘ ወረራና ጭፍጨፋ ሲፈፀም የቆየና አሁንም እየፈፀመ ይገኛል። በመላው አማራ በተለይም በጎጃም እያካሄደ ባለው ጭፍጨፋ ንጹሐንን በከባድ መሳሪያ ገድሏል፤ የአርሶ አደሩ አዝመራ እንደ ጧፍ እንዲነድ አድርጓል። የጤና ባለሙያዋችን ደብድቧል፤ በአርሶ አደር ቤት እየገባ ሽሮና በርበሬ ዘርፏል። በተለያዩ ድብቅ ቤቶች ወጣቶችን ረሽኗል፤ ሰላማዊ ሰዎችን በጅምላ በማሰር መፈታት ከፈለጋችሁ ብር ክፈሉ እያሉ በ100 ሺህ የሚቆጠር ብር ተቀብሏል። የተቀደሱ ቤተ እምነቶቻችን ውስጥ እየገባ ፀያፍ ሥራ ሠርቷል። በደረሰበት ኹለንታናዊ ድጋፍ የሚይዘው የሚለቀው የጠፋው የፋሽስቱ ኃይል አሁንም ተጨማሪ ኃይል በገፍ እያስገባ ሀገር ወዳዱን ሕዝባችንን በመጨፍጨፍ ላይ ስለሆነ፤ የዘወትር ሎጅስቲክስ አቅራቢያችን የኦሕዴድ ሠራዊት ያስገባውን ማቴሪያል እንደተለመደው እስክንቀበለው ድረስ ሌላ ተጨማሪ የፋሽስት ኃይል እንዳይገባ ለመከላከል ያግዘን ዘንድ ከነገ ማለትም ከኅዳር 12-03-2016 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከየትኛውም አቅጣጫ ከባጃጅና ሞተር በስተቀር ማንኛውም ተሽከርካሪ ላልተወሰነ ጊዜ እንዳይንቀሳቀስ የተወሰነ በመሆኑ አገር ወዳድ እና እንግዳ አክባሪው ሕዝባችን መጉላላት እንዳይደርስበት ይህን አውቆ እንዲንቀሳቀስ ስንል ለታታሪውና ሀገር ወዳዱ ሕዝባችን በአክብሮት እያሳወቅን፤ የተለመደ ትብብሩን ያደርግ ዘንድ እየገለፅን። ይህን ተላልፎ በሚገኝ በማንኛውም ተሽከርካሪ ላይ ለሚደርስበት ማንኛውም ድርጊት ግን ኃላፊነቱን አሽከርካሪዋች ወይም የአሽከርካሪ ባለሀብቶች የሚወስዱ መሆኑን እናሳስባለን ።

R:0 / I:0 / P:1 [R] [G] [-]

ከልጅ እያሱ ክፍለ ጦር የተሰጠ መግለጫ፣

የገጠመንን የህልውና ትግል ቀልብሰን ህዝባችን ለመታደግ ነፃነታችንን በክንዳችን ለማረጋገጥ ታሪካችን በእጆቻችን ለመፃፍ አንድ ሆነን ከመታገል ውጭ ሌላ አማራጭ አለመኖሩን አውቀን አንድነታችን አጠንክረን ጠላቶቻችን እንዳሰቡት ሳይሆን በተቃራኒው ድልን እየተቀናጀን እንገኛለን።ስለሆነም አጠቃላይ በደቡብ ወሎ ዞን ወረዳ ውስጥ የሚገኙ የፋኖ አደረጃጀቶች በብርጌድ ተደራጅተው ወደ አንድ ክፍለ ጦር በመምጣት የልጅ እያሱ ክፍለ ጦር በሚል ተቋቁሟል። በዚህ መሰረት የልጅ እያሱ ክፍለ ጦር የጋራ ስራ አስፈፃሚ በማዋቀር ሰባት ብርጌዶችን በመያዝ መመስርት ችሏል። የብርጌዶቹ ስምና የሚቀሳቀሱበት ቦታ እንድሁም አዛዥና ምክትል አዛዥ እንደሚከተለው ተቀምጠዋል።

1.ንጉስ ሚካኤል ብርጌድ

ዋና አዛዥ ፋኖ ሰለሞን አሊ

ምክትል አዛዥ ፋኖ አብይ ከበደ

የሚንቀሳቀስበት ቀጠናና

1.ደሴ ከተማ

2.ደሴ ዙሪያ ወረዳ

3 አልብኮ ወረዳ

4 ኩታበር ወረዳ

5.ኮምቦልቻ

2.አሳምነው ብረጌድ

መሪ ፋኖ ዶክተር ሙሉጌታ ድጋፌ

ምአዛዥ ሙሉጌታ የሺጥላ

የሚቀሳቀስበት ቀጠባ

1.አማራ ሳይንት ወረዳ

2.ሌጋምቦ ወረዳ

3.ቦረና ሳይንት ብሄራዊ ፓርክ

3.መቅደላ ብረጌድ

ዋና አዛዥ 50 አለቃ ሰይድ ሙሀመድ

ም/አዛዥ 10 አለቃ ጌትነት ታደሰ

የሚሽፍኑት ቀጠና

1. ማሻ ወረዳ

2. ተንታ ወረዳ

3.ቱላአውሊያ /ጊምባ

4.ሚንሊክ ብርጌድ

ዋና አዝዥ ፋኖ አብነው ታደሰ

ምክትል አዛዥ መቶ አለቃ በላይ መከተ

የሚንቀሳቀስበት ቀጠና

1.መካነሰላም (ቦረና) ወረዳ

2.ወግድ ወረዳ

3.ከለላ ወረዳ

5.ታዘበው ብረጌድ

ዋና አዛዥ ኑረድን

ምክትል አዛዥ ወልደ ታደሰ

የሚቀሳቀስበት ቀጠና

1,ጃማ ወረዳ

2,ወረኢሉ ወረዳ

3.ደገር

4.ለገሂዳ ወረዳ

6.ቴዎድሮስ ብርጌድ

ዋና አዛዥ ፋኖ አባተ ካሳነህ

ም/አዛዥ 100 አለቃ ተገኔ አለባቸው

የሚቀሳቀስበት ቀጠና

1.ኮምቦልቻ ከተማ

2.ተሁለደሬ ወረዳ (ሀይቅ)

3.ቃሉ ወረዳ

4 አምባሰል ወረዳ

5.ደላንታ ወረዳ

7.አትሮንስ ብርጌድ

ዋና አዛዥ ይታገስ አራጋው

ምክትል አዛዥ ሻምበል ጀምበሩ

የሚቀሳቀሳበት ቀጠና

1.መሀል ሳይንት ወረዳ

2.ቦረና ሳይንት ብሄራዊ ፓርክ

3.ሌጋምቦ ወረዳ

በዚህ አደረጃጀት ውስጥ የአማራን ህዝብ ህልውና ለማስከበር እና የመጣብንን ፈተና ለመቀልበስ እንድሁም አብሮን ለመታገል የሚፈልግ አካል በብርጌድ፣ በሻለቃና በሻምበል እየተዋቀረ ለሚመጡ እና አብሮን ለስራት ፋላጎት ያለው ሁሉ አብረን ለመስራት በራችን ክፍት መሆኑንና በክፍለ ጦሩ ስር ለመካተት ፍቃደኝነታችን ከወደሁ ለማሳወቅ እንወዳለን።

ድል ለአማራ ህዝብ

ዘላለማዊ ክብር ለትግሉ ሰማእታት‼

R:0 / I:0 / P:1 [R] [G] [-]

ለዓለማቀፍ ረድዔት ድርጅቶች የቀረበ የሰብዓዊ ዕርዳታ ድጋፍ ጥሪ

Facebook

ለዓለማቀፍ ረድዔት ድርጅቶች የቀረበ የሰብዓዊ

ዕርዳታ ድጋፍ ጥሪ

ከቴዎድሮስ ብርጌድ እና ከሰሜን አማራ ፋኖ

***

የአማራ ሕዝብ የገጠመውን የህልውና አደጋ

የመቀልበስ ተልዕኮ ይዞ ወደትግል ሜዳ የገባው ፋኖ የወጣበትን ሕዝብ ሰብዓዊ ሁኔታና ደህንነት

የመከታተል ብሎም የማረጋገጥ ኃላፊነት እንዳለበት

ያምናል። ፋኖ የአማራ ሕዝብ የገጠመውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ የማይተካ ሕይወቱን እየገበረ ለነፃነት፣ ለፍትሕና እኩልነት በመፋለም ላይ ይገኛል።

በቀዳሚነት የሚታገልለት የአማራ ሕዝብም

በየአካባቢው ራሱን እንዲከላከልና የህልውና አደጋ

ምንጭ የሆነውን የብልጽግና አገዛዝ ሰራዊትን በደፈጣ እረፍት እንዲነሳ የትግል ስትራቴጂ እየሰጠ ያነቃቃል ያስተባብራል። በዚህም ከራሱ ከሕዝቡ የወጣው ፋኖ፣ የሕዝብ ትግል መሪነቱን በተግባር በማሳየት ላይ ነው።

በዚህ የተናበበ ትግል ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገባው የብልጽግና አገዛዝ ሕዝባችንን በፖሊሲ ደረጃ

በመቅጣት ላይ ይገኛል። አገዛዙ በሕዝባችን ላይ

የከፈተው ጥቃት መልከ ብዙ ሆኖ ዋተኛው ጥቃቱ ግን ረሃብን እንደጦር መሳሪያ በመጠቀም የትግል ማሸነፊያ መንገድ ለማድረግ በማሰብ የጀመረው ሰብዓዊ እርዳታን የመንፈግ ጅምላ ጨራሽ ውሳኔው ነው።

ፋኖ በስፋት ከማንቀሳቀስባቸው ቀጠናዎች አንዱ

የሆነው የሰሜን አማራ አካባቢ፣ በሰሜን ጎንደር ዞን

ከሚገኙ 11 ወረዳዎች ውስጥ ዘጠኙ በከፊልና ሙሉ

በሙሉ ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል፤

ከእነዚህ ውስጥ በሁለት ወረዳዎች ማለትም ጃናሞራ

እና በየዳ ግልፅ ረሃብ ተከስቷል። በተለይም ጃናሞራ

13ቱም የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ ከፍተኛ ረሃብ

ተከስቷል። ምዕራብ እና ምሥራቅ ጠለምት

ወረዳዎችም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

የፋኖ ስትራቴጂ ጥናት ክፍል ከሲቪል አካላት ጋር

በመሆን ባሰባሰበው መረጃ መሰረት ድርቁ ወደረሃብ

ማደጉን ተከትሎ እስካሁን ከ120-135 የሚገመቱ

ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፣ አብዛኞቹ ሟቾች ወላድ

እናቶችና ህፃናት ናቸው። በሌላ በኩል በሰሜን ጎንደር

ዞን ብቻ ከ10,500 በላይ የዳልጋ እና የጋማ ከብቶች

በድርቁ ምክንያት ሙተዋል።

በሰሜን ጎንደር ዞን ብቻ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ዜጎች የዕለት ምግብ ረድዔት ጠባቂዎች ለመሆን ተገደዋል። ከእነዚህም ውስጥ 4000 ሺህ የሚሆኑት አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው በሕይወት እና በሞት መካከል የመጨረሻው እስትንፋስ ላይ የሚገኙ ግፉዓን ናቸው።

ከድርቁ ጋር በተያያዘ እንደ ኮሌራ እና አተት ያሉ

ወረርሽኞች ተከስተዋል። በመንግሥት አቅም መቅረብ ይችሉ የነበሩ የወረርሽኝ መከላከያ መድኃኒቶች እና የሕክምና አቅርቦቶች ሆን ተብሎ እንዳይቀርቡ በመደረጉ ሕዝባችን በረሃብና በወረርሽኝ እንዲሞት በመደረግ ላይ ነው።

አገዛዙ ለዚህ የሚሰጠው ምላሽ "ችግሩ ከአቅም

በላይ ሆኗል" የሚል ቢሆንም እውነታው ግን ረሃቡም

ሆነ ረሃቡን ተከትሎ የመጣው ወረርሽኝ የብልጽግና

ፖሊሲ ውጤት ነው። ሰብዓዊ ቀውሱ አድማሱን

እንዲያሰፋ የተፈለገውም ሕዝቡ የፋኖ ደጀን ነው

በሚል ሥርዓት ወለድ ጥላቻ እንደሆነ እናምናለን።

እነዚህ አካባቢዎች ዝናብ አጠር የሆኑ አካባቢዎች

ቢሆኑም ለዚህ መሰል የከፋ ችግር አልፎም የረሃብ

ተጋላጭነትን የሚያሰፋ ሰብዓዊ ቀውስ ደርሶባቸው

አያውቅም ነበር። የአሁኑ ሰብዓዊ ቀውስ የብልጽግና

አገዛዝ በአማራ ሕዝብ ላይ የያዘው ፀረ-አማራነት

ፖለቲካዊ አቋም ውጤት ነው።

በዚህም የብልጽግና አገዛዝ ረሃብን የጦር መሳሪያ

አድርጎ በመጠቀሙ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ዜጎች

በረሃብ የተነሳ ሕይወታቸው እያለፈ ይገኛል።

አሁን ለረሃብ የተጋለጡት አካባቢዎች ሰፊ የእንስሳት

ሃብት ያለባቸው እና ነዋሪዎችም በከፊል አርብቶ አደር በመሆናቸው የዛሬና የነገ ተስፋዎቻቸው የሆኑት የቤት እንስሳቶች እየረገፉ ነው።

በተመሳሳይ ሁኔታ የሰሜን ጎንደር ዞን አዋሳኝ የሆነው

ዋግ ኽምራ ዞንም የብልጽግና ፖሊሲ ውጤት የሆነ

ድርቅ ተከስቶ ዜጎች በረሃብ እየሞቱ፤ የአርሶ አደሮች

የቀንድና የጋማ ከብቶች እያለቁ ነው። በሰሃላ ሰየምት፣ ዝቋላ፣ አበርገሌ፣ ደሃና፣ … ወረዳዎችም ድርቁ አድማሱን አስፍቷል። አሳሳቢው ነገር ድርቁ ወደ ረሃብ ማደጉ ሲሆን፤ አገዛዙም ረሃብን የጦርነት ማሸነፊያ መሳሪያ አድርጎ እየተጠቀመበት ይገኛል።

እነዚህ አካባቢዎች ቀደም ሲል በሰሜኑ ጦርነት ተጎጅ

እንደነበሩ የሚታወስ ሲሆን፤ በአሁኑ ሰዓት እጅግ በከፋ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ።

በአጠቃላይ በተከዜ ተፋሰስ ስር በሚገኙ አካባቢዎች

ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የአማራ አካባቢዎች የብልጽግና አገዛዝ አማራን የማጥፋት ፖሊሲ አካል በሆነው በዕለት ደራሽ ምግብ ዜጎችን መቅጣት (ረሃብን የጦርነት ማሸነፊያ መሳሪያ ማድረግ) ፖሊሲው ሚሊዮኖች የዕለት ሰብዓዊ ዕርዳታ ጠባቂ ለመሆን ተገደዋል።

በዚህም ምክንያት ሕፃናትና ወላድ እናቶች በረሃብ

ሕይወታቸው እያለፈ ይገኛል። ስለሆነም ዓለማቀፍ የረድዔት ድርጅቶች በአማራ ግዛት በተለይም ችግሩ በከፋባቸው አካባቢዎች ተንቀሳቅሰው የዕለት ሰብዓዊ እርዳታ እንዲያደርጉ ፋኖ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ያረጋግጣል።

በመሆኑም፦

1) የዓለም ምግብ ፕሮግራም እና ዩኤስኤአይዲን

የመሳሰሉ የሰብዓዊ ረድዔት ድርጅቶች የብልጽግና

አገዛዝ ረሃብን የጦርነት ማሸነፊያ ስልት በማድረግ

ዜጎችን ወደሞት ጎዳና እየነዳ መሆኑን አውቃችሁ

የተቋረጠውን ድጋፋችሁን በፍጥነት እንድትጀምሩ

በሕዝባችን ስም እንጠይቃለን።

2) ፋኖ፣ የሰብዓዊ ረድዔት ድርጅቶቹ ለሥራቸው

አመችነት በተለይም ለሰራተኞቻቸው ደህንነት

አስፈላጊውን ሁሉ ጥበቃና ጥንቃቄ እንደሚያደርግ

ያረጋግጣል። በተለይም አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ

በሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች በፋኖ በኩል ምንም

ዓይነት ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንደማያደርግ ይልቁንም ለዚሁ ሰብዓዊ እርዳታ ዓላማ ጥበቃ እንደሚሰጥ ያረጋግጣል።

3) በአሁኑ ሰዓት በአማራ ክልል በተጠቀሱ

አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ፣ ወደረሃብ ያደገው

አገዛዙ ረሃብን እንደጦር መሳሪያ በመጠቀሙ ነው።

ይህ ሁኔታ አድማሱን አስፍቶ በመላ አማራ ክልል

ብሎም በመላ ኢትዮጵያ ሰብዓዊ ቀውሶችን አሁን

ካለንበት በከፋ መልኩ ከማባባሱ በፊት የዓለማቀፉ

ማኀበረሰብ በብልጽግና አገዛዝ ላይ ጫና እንዲያሳድር እየጠየቅን የድርቁን ሁኔታ በተመለከተ በአገዛዙ በኩል የሚቀርቡ ሐሰተኛ መረጃዎችን ውድቅ በማድረግ እውነታውን በባለሙያዎቻችሁ በኩል መሬት ወርዳችሁ እንድታረጋግጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

4) በአገር ውስጥ የምትገኙ አገር በቀል የእርዳታ

ድርጅቶችና በጎ ፍቃደኛ የሆናችሁ ግለሰቦችና ቡድኖች ለሰብዓዊ እርዳታው የምታደርጉትን ጥረት ፋኖ እያደነቀ፣ የብልጽግና አገዛዝ ረሃብን እንደጦር መሳሪያ እየተጠቀመ ስለመሆኑ በተጨባጭ ማስረጃዎች እንድታጋልጡ ጥሪውን ያቀርባል።

***

ረሃብን የጦር መሳሪያ በማድረግ የሚቀለበስ የአማራ

ትግል የለም!!

የቴዎድሮስ ብርጌድ እና የሰሜን አማራ ፋኖ

መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ.ም

R:0 / I:0 / P:1 [R] [G] [-]

ከአማራ ፋኖ አንድነት በሸዋ የተሠጠ መግለጫ

ከአማራ ፋኖ አንድነት በሸዋ የተሠጠ መግለጫ..‼️‼️

አማራን በመግደል በማፈናቀል እና የተለያዩ አሰቃቂ ግፎችን በመፈፀም የአማራን ህዝብ ከሦስት አስርት አመታት በላይ የመከራ ዶፍ በማውረደ አንገት አስደፍቶ መግዛት አይቻልም፡፡ሽንፈትንና ውርደትን የተከናነበው ፋሽስታዊ የአብይ አህመድ ቡድን ለረጂም አመታት የአማራን ህዝብ በጥላትነት በመፈረጅ በአስተሳሰቡ፣ በኢኮኖሚ እና በስነ

ልቦናው የበታች አድርጎ መግዛት በስርአተ ትምህረት ጭምር በመታገዝ የተለያየ የማስፈፀሚያ ስልቶች በመጠቀም ዛሬ የምናየው የአማራን የፍትሃዊነት ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የመኖር ያለመኖር ዋስትና ጭምር በመንፈግ የአንድ ሃገር መከላከያ

ሰራዊት ታሪካዊ ተቀባይነት በማሳጣት የአንድ ዘረኛና ፅንፈኛ ሃገር አፍራሽ ቡድን ሃሳብ ተሸካሚ በማድረግ በመላው የአማራ ህዝብ ላይ ዛሬ የምናየውን ስር ነቀል ዘር የማጥፋት ዘመቻ እየፈፀመ መሆኑ አለም የሚያውቀው የገሃዱ አለም ሆኗል፡፡ለዚህም እንደ ማሳያ ባለፍው ሣምንት ብቻ በአማራ ክልል በሸዋ ህዝብ ላይ የሃገር መከላከያ ነኝ በሚለው አካል

የተከናወኑ የግፍ ተግባራት፡-

1ኛ. በተሬ ቀበሌ ጤና ጣቢያ ውስጥ በመግባት

መድሃኒቶችን መዝረፍና የአገልግሎት መስጫ መሳሪያዎችን ሙሉ ለሙሉ ማውደም፣ የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር በጥይት በመምታት ኤሌክትሪክ እንዲቋረጥ ማድረግ፣ የአርሶ አደር በሬዎችን መዝረፍና አርዶ መብላት

2ኛ. በራሳ ቀጠና በጅምደሬ ቀበሌ ለእረኝነት የተላኩ ዘጠኝ የአርሶ አደር ህፃናት ልጆችን እጃቸውን ወደኋላ በማሰር ጫካ ውስጥ መረሸን፡፡ በዚያው ቀጠና ኩሬበረት፣ አባያጥር፣ ሂዲ፣ ግልጥበረት፣ እንዲሁም ሰፊበረት አንድ አዛውንት አስረው በገጀራ አንገቱን ቆርጠው ገለዋል፡፡ አንድ ወጣት ልጅ ገድለው እንጨት ላይ ሰቅለዋል፡፡ የግለሰብ ንብረቶችን

መኪና በማሰጠጋት ዘርፈዋል፣ ቤትና ንብረትን አቃጥለዋል፡ በርካታ ግመሎችን ገለዋል፤ በሬዎችንና ፍየሎችን አርደው

በልተዋል፡፡ መዲና ቀበሌ በየቤቱ በመግባት ሽሮና በርበሬ፣

ዱቄት ወስደዋል ዶሮና ፍዬል አርደው በልተዋል፡፡

3ኛ.በመንዝ ቀያ ወረዳ ስድስት ታዳጊ ሴት ልጆችን ባሰቃቂ

ሁኔታ ደፍረው በጅምላ ገድለዋቸዋል፡፡

4ኛ. በአንኮበር ወረዳ ቁንዲ ቀበሌ የግለሰብ ጥንድ

በሬዎችን አርደው ከበሉ በኋላ በግፈ ገድለዋል፡፡

5ኛ. በኤፍራታና ግድም ወረዳ ማጀቴ ቀበሌ ህዝብ ላይ

የፈፀሙት ሴቶችንና ህፃናት የችግሩ ሰለባ ያደረገ የጅምላ

ግድያ መፈፀሙ አበይት ማሳያ ናቸው፡ይህን ፋሽስታዊ

ተግባር ለመቀልበስ አቅዶና አልሞ መስራት እንዳለበት

ቀድሞ የተገነዘበው የአማራ ፋኖ አንድነት በሸዋ ከዚህ

በታች ያሉትን በአንድ ኮማንድ የሚመሩ ብርጌዶችን

በማቋቋም የተጠናከረ ማጥቃት ለማድረግ ዝግጅቱን

ጨርሷል፡፡

1ኛ. በይፋት ቀጠና ደጃዘማች ተሰማ እረገጤ ብርጌድ

2ኛ. በግሸና አካባቢው አሳምነው ፅጌ ብርጌድ

3ኛ. በመንዝ አካባቢ ሚኒሊክ ብርጌድ

4ኛ. ደብረብርሃን እና ዙሪያው መብረቁ ብርጌድ

5ኛ. በመረሃቢቴ ቀጠና አስማረ ዳኜ ብረጌድ

6ኛ. በአንኮበር እና አካባቢው ጣይቱ ብርጌድ

7ኛ. በጅሩ ራስ አበበ አረጋዊ ብርጌድ

መቋቋሙን በይፋ እያሳወቅን ከዚህ በታች ያለውን የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡፡

1ኛ. በአማራ ክልል የምትገኙ የአማራን ስመ ልብስ ለብሳችሁ አማራን ለመውጋት የተዘጋጃችሁ አድማ በታኝ እና አንዳንድ ሰላም አስከባሪ ነን ባዮች ወደ ማይቀለበሰው የአማራ ትግል እንድትቀላቀሉ ተደጋጋሚ ጥሪ ማቅረባችን ይታዎቃል፡፡

2ኛ. ዛሬም የብልፅግና መዋቅር ለመመለስ ከቀበሌ እስከ ዞን ያላችሁ የብልፅግና ካድሬዎች/ ሆድ አደሮች እያደረጋችሁት ያለውን የአማራ ህዝብን የማጥፋት እንቅስቃሴ በቅርበት እየተከታተልን መሆኑን እየገለፅን ወደ ማህበረሰባችሁ እንድትመለሱ ስንል ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር የተለመደውን የፋኖ ውሳኔ ለመቀበል እንድትዘጋጁ እናሳስባለን፡፡

የአማራ ፋኖ አንድነት በሸዋ ዋና አዛዥ ሻለቃ መከታው ማሞ

R:0 / I:0 / P:1 [R] [G] [-]

የጎጃም ፋኖ ዕዝ በአንድ ዕዝ እየተመራ ነው !

የጎጃም ፋኖ ዕዝ በአንድ ዕዝ እየተመራ ነው !

ሰሞኑን የአማራን ህዝብ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ

ቀጥቅጦ ለመግዛት ቀነ ገደብ አስቀምጦ ቆርጦ የተነሳው ዐብይ አህመድ በሀገሪቱ አለ የተባለውን ጦር ወደ አማራ ክልል በዋናነት ወደ ጎጃም ማስገባቱ ይታወቃል ።

ሆኖም የጎጃም ፋኖ እና ህዝቡ ይኼንን ነፍሰ ገዳይ ሰራዊት ግንባር ለግንባር እየተፋለመው ይገኛል።

ጠላት የጎጃም አማራን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ

ለማንበርከክ ሁሉንም የመገናኛ ዘዴዎች አጥፍቶ በየቦታው ጦር አስገብቷል ።

የጎጃም ፋኖ እስከ አሁን ከመጣበት አስደናቂ ተጋድሎ ልምድ በመውሰድ ትግሉን ወደ ሌላ ከፍ ያለ ምዕራፍ ለማሳደግ በማሰብ ጎጃም ምድር የገባውን ጦር ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ አደረጃጀቱን ከፍ አድርጎ የጎጃም ፋኖ ዕዝ ወታደራዊ ክንፍ በአንድ ዕዝ እንዲመራ ውሳኔ ላይ ተደርሷል።

ወታደራዊ ክንፉ በአንድ ዕዝ እና አራት ኮሮች ይመራል፤ አምስት ታዋቂ ወታደራዊ መኮንኖች ይመሩታል።

እነዚህ ወታደራዊ መኮንኖች በመከላከያ ሰራዊት እና

በአማራ ልዩ ኃይል ውስጥ በከፍተኛ ወታደራዊ አቅም

የውጊያ ብቃታቸው የተመሰከረላቸው የብርጌድ እና ክፍለ ጦር መሪዎች የነበሩ ስመጥር መኮንኖች ናቸው ።

ጠላት ህዝቡን ለመጨፍጨፍ በየአካባቢው በኮር የተደራጀ ጦር በማስገባቱ ኮርን በኮር ለመመከት የጎጃም ፋኖ ዕዝ የኮር አመራሮችም በወታደራዊ ብቃታቸው በልዩ ልዩ ግንባሮች ተፈትነው ያለፉ እምቅ ወታደራዊ ችሎታ ያላቸው ስመ ጥር መኮንኖች ይመሩታል።

R:0 / I:0 / P:1 [R] [G] [-]

የፋሽስቱ የአብይ አህመድ ብሄራዊ የጸጥታ ምክር ቤት አማራን ለመጨፍጨፍ ያወጣው የውጊያ እቅድ

የፋሽስቱ የአብይ አህመድ ብሄራዊ የጸጥታ ምክር ቤት

አማራን ለመጨፍጨፍ ያወጣው የውጊያ እቅድ

=======

ፋሽስቱና ሰው በላው አብይ አህመድ የጸጥታ መዋቅር

የአማራ ህዝብ በጭካኔ ለማረድ የሚከተሉት የውጊያ

እቅዶች አውጥቷል

1ኛ. በወልቃይት ግንባር ከኤርትራ ጋር የለውን ወሰን በአየር

ወለድ: ኮማንዶ: ሜካናይዝድና በድሮን በመታገዝ በሩን

መዝጋትና ለአማራ የነፃነት ተዋጊዎች ምንም ዓይነት እርዳታ

ከኤርትራ እንዳይደርስ ማድረግ:: በዚህ ግንባር የወልቃይት

ህዝብ ሊዋጋን ይችላል በሚል ስጋት የትግሬ ወራሪ ኃይል

እንደ አማራጭ መጠቀምና ትህነግ በሽሬ ግንባር

በተጠንቀቅ እዲቆም ማድረግ:: እንደ አስፈላጊነቱ በኤርትራ

ላይም ከትህነግ ጋር በጋራ ማጥቃት ለመክፈት ተቅዷል::

2ኛ. የአማራ ህዝብ የዞን ከተሞችን በአየር ወለድና

በኮማንዶ ተዋጊዎች ብቻ የውጊያ ማድረግ:: በሁሉም የዞን

ከተሞች ኮማንዶና ብረት ለበስ ተዋጊዎች መንገድ ከሚመሩ

የብአዴን የከተማ ከንቲባዎች ጋር በመጣመር ከተማ ውስጥ

ያለን ህዝብ መጨፍጨፍና ውጊያውን በኮማንዶና ብረት

ለበስ ብቻ እንዲሆን ወስኗል

3ኛ. የወረዳ ከተማዎችንና የገጠር ከተሞችን የመከላከያ

እግረኛ ኃይል: አድማ በታኝ: ሚሊሻና ተላላኪ ባንዳ

አመራርን በመንገድ መሪነት በመጠቀም በገጠሩ ያለውን

ፋኖ በሽምቅ ውጊያ መዋጋት:: የገጠሩን ፋኖ ለመዋጋት

ለሚሊሻና ለካድሬዎች ከፍተኛ ገንዘብ በመክፈል መንገድ

መሪ ማድረግ:: አልዋጋም ብሎ የሚያፈገፍግ ሚሊሻና

አድማ ብተና ካለ መከላከያ ከሗላ ሁኖ እርምጃ

እንዲወስድበት ተወስኗል:: ሁሉም የዞንና የወረዳ አመራር

ውጊያውን በመምራት እንዲሳተፍ ቀጭን መመሪያ

ተላልፏል!

4ኛ. በወረዳና በገጠር ከተሞችና ቀበሌዎች በፋኖ ስም

ዝርፊያ የሚፈፀም ኃይል ማደራጀትና ህዝቡ እንዲማረርና

ፋኖን እንደ ዘራፊ እንዲቆጥረው ማድረግ:: ፋሽስቱ

የሚያደራጃቸው ቡድኖች ባንክ የሚዘርፉ: የኃይማኖት

ተቋማትን የሚዘርፉ: መንገድ ላይ መኪና አስቁመው

የሚዘርፉ እንዲሆኑ ተደርጎ እንዲደራጅ ተውስኗል

5ኛ. የወረዳና የገጠረ ከተማችን የመብራት መስመሮች በፋኖ

ስም በመቁርጥ የከተማ ነዎሪዎች የመብራት: የስልክና

የውሃ እገለግሎት እንዳያገኙ በማድረግ ህዝቡን ማማረር::

በገጠር አካባቢ በሚውሉ ክፍት የገበያ ቦታዎች ላይ ተኩስ

መክፈት: የግለሰብ መሳሪያዎችን የሚቀማ የአካባቢውን

ሰው መመልመልና አማራውን እርዕስ በርሱ ማገዳደል:

ሰዎችን የሚገድልና ሴቶችን የሚደፍር ኃይል ማሰማራት

የጦርነቱ አካል እንዲሆን ተደርጏል

6ኛ. በቴሌቪዥንና በማህበራዊ ሚዲያ እራሳቸው

አቀናብረው በህዝቡ ላይ የሚፈፅሙትን ወንጀል ፋኖ አደረገ

በማስባል ሚዲያውን መቆጣጠርና ህዝቡን ማደናገር:

ማወናበድ ወዘተ በከፊል የጦርነቱ ዕቅድ እንዲሆኑ

ተወስኗል::

ማሳሰቢያ:

አንዳንድ ወሳኝ መረጃዎችን ለፋኖ ጠቅላይ መምሪያ ብቻ

ስለሚያገለግሉ አልጠቀስኳቸውም::

መፍትሄዎች

==

ጀግናው የአማራ ህዝብ ሰራዊት ፋኖ በየትኛውም አካባቢ

ያለን ባንዳ ያለ ምንም ምህረት እርምጃ መውሰድ:: ስልጠና

የሚሰለጥንን ሚሊሻ ያለ ምንም ምህረት እርምጃ

መውሰድ:: ለምሳሌ ደቡብ ወሎ ከፍተኛ ሚሊሻ እያሰለጠነ

ነው: ይህንን መንጋ ያለ ምንም ምህረት እርምጃ መወሰድ::

ከእናንተ ጋር ነን እያሉ የሚያሾከሹኩ ባንዳዎች ላይ ምህረት

የለሽ እርምጃ መውሰድ:: ቴዎድሮስን የመሰለ ጀግና

ደብረታቦር ላይ: ክሩቤልን የመሰለ ጀግና ጎንደር ላይ

የገደለብን ባንዳ ነው!

ሌላው የአማራ ህዝብ አንድነቱን ማጠናከርና ለጠላት

ፕሮፖጋንዳ ሳይሸበር በጀግንነት መዋጋት ይጠበቅበታል!

እያንዳንዷን እንቅስቃሴ እየተከታተልን ለህዝባችን መረጃ እናቀርባለን!

ድለ ለታላቁ የአማራ ህዝብ!!!

R:0 / I:0 / P:2 [R] [G] [-]

Amhara Hero Aschalew Dese

Amhara Hero Aschalew Dese

R:0 / I:0 / P:2 [R] [G] [-]

𝐄𝐧𝐠𝐥𝐢𝐬𝐡 𝐭𝐫𝐚𝐧𝐬𝐥𝐚𝐭𝐢𝐨𝐧 𝐨𝐟 𝐭𝐡𝐞 𝐡𝐢𝐠𝐡𝐥𝐲 𝐜𝐥𝐚𝐬𝐬𝐢𝐟𝐢𝐞𝐝 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚𝐧 𝐦𝐢𝐥𝐢𝐭𝐚𝐫𝐲 𝐝𝐨𝐜𝐮𝐦𝐞𝐧𝐭 𝐭𝐡𝐚𝐭 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝟑𝟔𝟎 released 16/01/2016 Ethiopian Calendar (September 27/2023)

The document is from a meeting top Ethiopian military officials had with top government officials. It gives an assessment of the achievements and challenges faced by the Ethiopian National Defense Force (ENDF) in Amhara region. Note: They don’t call Fano by its name in this document, referring to it as “extremist group” or “this group”. Anything in brackets () was not in the document and is only there to give context.

𝐀𝐜𝐡𝐢𝐞𝐯𝐞𝐦𝐞𝐧𝐭𝐬 𝐚𝐧𝐝 𝐅𝐚𝐢𝐥𝐮𝐫𝐞𝐬 𝐨𝐟 𝐭𝐡𝐞 𝐖𝐚𝐫 𝐢𝐧 𝐀𝐦𝐡𝐚𝐫𝐚 𝐫𝐞𝐠𝐢𝐨𝐧: 𝐂𝐡𝐚𝐥𝐥𝐞𝐧𝐠𝐞𝐬:

1. The extremist group (Fano) is decentralized so that has made it a challenge to finish this operation quickly. Its lack of centralization makes it’s hard to finish the law enforcement operation in a timely manner.

2. In some places this group has so much public support, it’s hard to root it out from the people.

3. This group has infiltrated the government institutions so deeply that they have managed to avoid ENDF operations by getting information ahead of time.

4. This groups' guerrilla warfare and ambush’s on the army has caused extensive damage and disrupted our supply lines.

5. These sustained attacks have caused exhaustion and division within ENDF.

6. The people (Amhara) have been subject to so much propaganda, that they now see the Ethiopian army as an enemy and are supporting the group.

7. The newly established regional administration has not setup its zonal and wereda administration at the speed it’s expected to.

8. Some of the  extreme actions we took (war crimes), with legal backing of the state of emergency, to put fear in the people has been secretly recorded and released, damaging ENDFs good reputation.

9. Our shelling of homes and places of worship in some of the urban fightings has made the people suspicious of us.

10. Our troops that were sent into cities for assessment have been accused of rape and looting by the people. We’ve received multiple complaints. People have tried to protest in some places where our troops were accused of rape. 11. In some places, farmers have started fighting ENDF after their crops sustained damages by the army.

12. The drastic increase in prices of produce in cities due to supply shortages, might cause an uprising from the people.

13. The group (Fano) might start to get support from civil servants, who are not getting paid at the moment.

14. We’ve been able to confirm from our public meetings with people throughout the region that neither the previous administration nor the current administration has the support of the people. The extremist group might wait for an opportune moment to attack the new administration.

15. The members of the new regional administration are suspicious of each other and don’t seem to have to capability to coordinate and work together.

16. The government employees within the region believe that the extremist group (Fano) is raising a legitimate question of the people, and are not taking orders of the new administration.

17. The questions the farmers have raised in regards to fertilizers and other supplies not being met has angered them and the protests might continue in the future.

18. International Pressure: - Our army is getting similar accusations it was getting during the war in Tigray. - Our historical enemies might use this opportunity to attack us. - The groups' (Fano) diaspora supporters might continue to protest and work to get Western governments to put pressure on the Ethiopian government. 𝐀𝐜𝐡𝐢𝐞𝐯𝐞𝐦𝐞𝐧𝐭𝐬:

1. After the law enforcement operation was started, we have managed to dislodge the looting group (Fano) out of the main cities and zones.

2. We prevented the regional coup attempt and have allowed the transition of power from the previous administration to the new one.

3. We’ve managed to open the major highways that go from Gojjam to Addis Ababa and the ones from Dessie and Debreberhan to Addis, allowing the flow of goods and alleviating the cost of goods increase.

4. The disrupted flights to the major cities have been restored.

5. We’ve curtailed the free movement of the enemy and its ability to communicate. 6. Action is being taken against the groups financiers. 𝐏𝐥𝐚𝐧𝐬 𝐭𝐨 𝐛𝐞 𝐭𝐚𝐤𝐞𝐧 𝐦𝐨𝐯𝐢𝐧𝐠 𝐟𝐨𝐫𝐰𝐚𝐫𝐝:

1. We have to disrupt the public support this extremist group enjoys in the region. This group is responsible for looting, raping, and destroying infrastructure, and we have to make the people of the region aware of their crimes.

2. Since there is a large segment of people that believe this group believes in the superiority of one religion (Orthodox), we need to find different ways to amplify these people’s suspicions. (Create Christian Muslim divide).

3. We need to make nations and nationalities in Ethiopia aware that this group is anti Ethiopia and wants to swallow the different nations and nationalities and bring back the old unitary government.

4. We have to show people that this group is an obstacle to the prosperity journey that Ethiopia has started, and is getting support from our historical enemies (Egypt or Eritrea???).

5. We have to disrupt the groups unity and create internal division. Since the group has some issues with finance distributions, we have to use social media to amplify these problems. We have to infiltrate and sway some of the low level leaders of the group and have them work for us. Since there might be some differences between the top leaders of this group, we have to do more research to identify these differences and exploit them.

6. We have to eclipse the upper hand the group has on the propaganda war. - We have to identify the groups' Facebook army leaders and take action against them. - We have to do research on the YouTube channels that are releasing information and take action against them. - We have to take action against people who talk about the groups bravery in grocery stores and restaurants. - We have to take action against any drivers or business owners that have stickers or display of the group.

7. We have to have sustained discussions with the public. - We have to have discussions with the group’s (Fano's) core support base, the farmers, and persuade them to be on our side. - Continue and expand the discussions we’re having with the people in cities. - Identifying the people that show ideological support to the group at these public meetings and taking action against them. - We have to get famous people, wealthy people, artists, religious leaders, Aba Gadas, and politicians to publicly condemn this group (Fano). New military strategy to follow:

1. Use new technology to search and take action against the group’s (Fano) major military tactic of ambush attacks.

2. Using police and local militia that are familiar with the environment. 3. Strengthening the regions Protest Disruption Police force.

4. Identify the areas the group (Fano) uses for hiding and use air strikes to attack them.

5. Deploy the Republican Guard in major cities in order to disrupt the group’s (Fano) attack on cities.

6. Send famous artists and bands to the military camps throughout the region to tackle the demoralization and exhaustion of the army.

7. Give encouragement to the Colonels and low level leaders within the army.

8. Take decisive action against ENDF soldiers that try to surrender to the group (Fano) or try to desert the army. Conclusion: Actions that will speed up the law enforcement operation in Amhara region:

1. Cutting off telecommunications, power, and banking for a “brief” period of time to put pressure on the people and exhaust them so they can turn on the group (Fano) and fight on our side.

2. Taking decisive action against those within the government that are colluding or providing intel to the group (Fano).

3. Taking successive, technology supported, military operations against the group (Fano).

4. Start a nation wide campaign to mobilize the people to give moral and material support to the army.

R:1 / I:1 / P:2 [R] [G] [-]

እኔ ፋኖ ነኝ

ድል ለፋኖ

I am Fano

Victory to Fano