[ / / / / / / / / / / / / / ] [ dir / random / 93 / biohzrd / hkacade / hkpnd / tct / utd / uy / yebalnia ]

/ethiopiaoneamhara/ - UNITED ETHIOPIA ONE AMHARA

ONE AMHARA ONE ETHIOPIA

Name
Email
Subject
REC
STOP
Comment *
File
Password (Randomized for file and post deletion; you may also set your own.)
Archive
* = required field[▶Show post options & limits]
Confused? See the FAQ.
Options

Allowed file types:jpg, jpeg, gif, png, webp,webm, mp4, mov
Max filesize is16 MB.
Max image dimensions are15000 x15000.
You may upload1 per post.


File: daf1adabdde7432⋯.jpg (58.35 KB,720x539,720:539,img_1_1710438269605.jpg)

 No.19

የአማራ ፋኖ በጎጃም መግለጫ የ ድማማ ዴክላሬሽን

'ከአማራ ፋኖ በጎጃም" የተሰጠ መግለጫ

(ድማማ ዲክላሳሬሽን)

የአማራ ሕዝብ በፋሽስቱ የብልጽግና ስርዓት በተደቀነበት የህልውና አደጋ እና ከተከፈተበት ሁሉን አቀፍ ጥቃትና ወረራ ራሱን ከመከላከል ወደ ተሟላ በትጥቅ ትግል የሚደረግ ጠላትን ማሸነፍ፤ በመላው ኢትዮጵያዊያን ፈቃድ የሚመሰረት አዲስ ስርዓት ለማዋለድ በከፍተኛ የድል ግስጋሴ ላይ መሆኑ ታዉቆ ያደረ ጉዳይ ነው፡፡ ይህንንም በከፍተኛ የእሳቤ እና ድርጀታዊ ጥንካሬ መምራት በውል እየተተገበረ እና በሚመጥን መልኩ እየተጠናከረ እየሄደ ያለ ነው፡፡

ትግሉ አሁን ባለበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ የአምበሳውን ድርሻ እየተወጡ ያሉ የፋኖ አደረጃጀቶች የዓላማ እና የተልዕኮ ልዩነት ባይናራቸውም አንድ ወጥ መዋቅራዊ ቅርፅ መያዝ አለመቻላቸው በትግሉ ሂደት እና ፍጥነት ላይ የፈጠረው ሳንካ በቀላሉ የሚታይ አለመሆኑን በትግሉ ዛሂደት ከገጠሙን ችግርች መረዳት ችለናል፡፡

የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ከተመሰረተበት ዕለት ጀምር' ባከናወናቸው ተጋድሎዎች ደማቅ ታሪክ የጻፈፊ ሲሆን የፋኖን እንቅስቃሴ በማሰልጠን፤ በማደራጀት፤ ማስታጠት እና ማታገል ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ የአማራ ሕዝብ ተጋድሉ እና የፋኖ ሠራዊት እድገት የወለደው የጎጃዛም እዝ ፋኖም ትግሉን ወደ ከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ረገድ ያደረገው አስተዋፅኦም በታሪክ ፊት የሚታወስ ነው፡፡

አሁን ባለንበት ነባራዊ ሁኔታ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ እነኝህን ስሞች መጠቀም አስፈለጊ ሆኖ አለመገኘቱን እና ትግሉን በተቀናጀ የአመራር ስምሪት መምራት እና ለዚህም መገዛት የሚገባን ስለመሆኑ የህዝባዊ ኃይሉም ሆነ የእዙ አመራሮች ከተደጋጋሚ ውይይቶች በኋላ በሙሉ ድምፅ አምነንበታል።፡ ይህንንም ስምምነትና ውሳኔ "ድማማ ዲክላሬሽን" በሚል ሰይመነዋል፡፡

ይህንን የአደረጃጀት ጉዳይ እልባት ለመስጠት የተለያዩ ወገኖቻችን ከሚያደርጉት ጥረት ጎን ለጎን እኛም ለሶስት ግዜያት ያህክል ፍፁም ወንድማማችነት፤ አማራዊ ጨዋነት እና ኢትዮጵያዊ ግብረ ገብነት በተላበሰ መልኩ ባደረግነው ውይይት መሰረት አንድ መዋቅር እና አመራር የሚፈጠርበትን

ሁኔታ ለማምጣት ተስማምተናል፡፡

ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረስነው ትግሉ የደረሰበት ደረጃ፤ ቀጣይ የሚጠበቅብን ከፍተኛ ኃላፊነት፤ ይህንን ትግል የተሻለ ደረጃ ላይ ደርሶ ማዬት የሚፈልጉ የፋኖ ሰራዊት አባላት፤ ሌሎች አቻ

የፋኖ አደረጃጀቶች፤ በውጭ እና በሀገር ውስጥ ያሉ ደጋፊዎች ለጉዳዩ ያላቸውን ጉጉት እና ፅኑ ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት የሁለቱም ወገን አመራርች በአንድነት የሚመሩትን የፋኖ አደረጃጀት ማምጣት እጅጉን አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ ነው፡፡

በዚህም መሰረት "የአማራ ፋና በጎጃም" በሚል መጠሪያ ወደ አንድና ወጥ የፋና አደረጃጀት ማሳደጋችንን ለመላው የሰራዊት አመራርና አባላት፤ ለመላው የአማራ ህዝብ እና ኢትዮጵያዊያን

አንዲሁም ደጋፊዎቻችን ሁሉ ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው።፡

በመሆኑም "የአማራ ፋኖ በጎጃም" ቀጥሉ የተዘረዘሩትን ጥሪዎች ያቀርባል፡-

1/ ይህ መግለጫ ከተሰጠበት እለት ጆምሮ በነባር አደረጃጆቶች ስር የሚንተሳተሰው የፋኖ ሰራዊት

“የአማራ ፋኖ በጎጃም” አመራር እና አባል መሆኑን አውቆ በዚሁ መጠሪያ እንዲጠቀም እያሳሰብን ማዲያዎችም ከዚህ ዕለት ጀምሮ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል እና የጎጃም እዝ ፋኖ የሚሉትን አጠራሮች እንዳይጠቀሙ በዚህ ፋንታ "የአማራ ፋኖ በጎጃም" የሚለውን ስም ብቻ እንዲጠቀሙ እናሳስባልን፡፡

2/ አንድ መዋቅር እና አመራር ለመፍጠር በተደረገው ውሳኔ መሰረት የአማራ ፋኖ በጎጃም አመራሮች;

1. አርበኛ ዘመነ ካሴ - ሰብሳቢ፤

2. ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው - ም/ሰብሳቢ እና ወታደራዊ አዛዥ

2.1. ሻለቃ የኔዓለም ዘለቀ - ም/ወታደራዊ አዛዥ

22. ዘመቻ ኃላፊ - መ/አ አበበ ሰው መሆን

23. ም/ዘመቻ ኃላፊ - መ/አ ማርቆስ አሞኘ

2.4. ስልጠና ኃሳፊ - ፃ/አ ታዬ ብርሐኑ

2.5. ም/ስልጠና ኃላፊ - ኮ/ል ጌታሁን መኮንን

2.6. ሎጀስቲክስ ኃላፊ - ዘመነ- ገረመው

2.7. ም/ሎጀስቲክስ ኃላፊ - መንበሩ ጌታዬ

2.8. ወታደራዊ አስተዳደር - ዛ/አ ይበልጣል መልካሙ

3. አርበኛ እና ጠበቃ አስረስ ማረ ዳምጤ - ም/ሰብሳቢ እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ

3.1. ግሩም ምሳሌ - ም/የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ

4. የውጭ ግንኙነት እና የዲያስፖራ ጉዳዮች መምሪያ -

4.1. ስሜነህ ሙላቱ - ኃላፊ

4.2. ኃ/ሚካኤል ባዬ - ም/ኃላፊ

5. የቀጠናዊ ትስስር መምሪያ -

5.1. የቆዬ ሞላ - ኃላፊ

5.2. አዲሱ ፈጠነ - ም/ኃላፊ

6. የህዝብ ግንኙነት መምሪያ

6.1. ማርሸት ፀሐው - ኃላፊ

6.2. ዮሐንስ አለማየሁ - ም/ኃላፊ

7. ስትራቴጂክ ጉዳዮች መምሪያ

7.4. ተሰማ ካሳሁን - ኃላፊ

7.2. ጎበዜ ጌታሁን - ም/ኃላፊ

8. የፋይናንስ እና ንብረት አስተዳድር መምሪያ

8.1. ማንችሎት እሱባለው - ኃላፊ

8.2. ዳኛው ሽባባው - ም/ኃላፊ

9. የ፳/ቤት ኃላፊ

9.1. ይትባረክ አንዳርጌ - ኃላፊ

9.2.- በለጠ አብርሐም - ም/ኃላፊ

10. የአደረጃጀት ዘርፍ መምሪያ

10.1. አሸቱ ጌትነት - ኃላፊ

10.2. ስለሺ ከበደ - ም/ኃላፊ

11. መረጃ እና ደህንነት መምሪያ - xxx

ሆነው እንዲመሩ ተስማምተናል፡፡

3/ ይህ መግለጫ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ' የሚሰበሰብ የሉጅስቲክስ እና የፋይናንስ ድጋፍ “የአማራ ፋኖ በጎጃም" በሚሰጠው መመሪያ እና ለዚሁ ጉዳይ በሚያደራጀው መምሪያ (የስራ ክፍሎች) መሰረት እንዲፈፀም እና በዚህ አግባብ እንዲከናወን መወሰናችንን እናስታውቃለን፡፡ ሁሉም መዋቅራዊ ጉዳይ በተመሳሳይ አካሄድ የሚፈፀም ይሆናል፡፡

4/ ለመላው የአማራ ህዝብ እና ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በዚህ ውሳኔያችን መሰረት ኃይላችንን በማጠናከር ለምንፈጽመው ከፍተኛ ጠላትን የማሽመድመድ እና ወደ ድል የመገስገስ ሂደት በሙሉ ልብ እና ቀና ፍላጎት ከጎናችን በመሰለፍ ይህንን ሀገር እና ህዝብ ጠል ጥገኛ ፋሽስት ስርዓት በማስወገድ ለፍትሕ እና እኩልነት የቆመ አዲስ ኢትዮጵያዊ ስርዓት ለመመስረት ዝግጁ እንድትሆኑ ብርቱ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

5/ በሌሎች የአማራ ክፍለ ግዛቶች እና ቀጠናዎች ያላችሁ የፋኖ አደረጃጀቶች እንደ አንድ አማራ ልንሰራ ያቀድነውን እና እየደከምንበት ያለውን አንድ ወጥ ደርጅት ለመፍጠር ለምናደርገው ርብርብ እና ወንድማዊ ጥሪ ራሳችሁን አንድታዘጋጁ እና በፍጥነት የጋራ ቤታችንን እንድንቀልስ

ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ይህም የትግላችን ወሳኙ ምዕራፍ ነው፡፡

6/ ለትግሉ አበርክቶ ያለው የተለያየ አቅም፤ ሙያ እና ፍላጎት ያላችሁ ምሁራን ያለንበትን የህልውና ትግል መቀላቀል ታሪካዊ የውዴታ ግዴታችሁ መሆኑን ተገንዝባችሁ እና ድርጅታችን

አቅም እና ፍላጎቱ ያለውን ሁሉ የሚያስተናግድበት መደላድል እንዳለም አውቃችሁ ትግሉን እንድተቀላቀሉ እናሳስባለን፡፡

7/ በመጨረሻም ትግላችን የደረሰበትን ደረጃ በውል መገንዘብ እንደሚገባ እየገለጽን ይህ አደረጃጀት የምንታገልለትን ህዝብ፤ የትግሉን ደጋፊዎች፤ የሰራዊታችንን ወቅታዊ ፍላጎት በአጠቃላይ ጊዜው የጠየቀውን የመዋቅርና አመራር ማጠናከር ታሳቢ አድርገን በቅንነት ያዋለድነው አደረጃጀት መሆኑን የሚመለከተው ሁሉ እንዲረዳው እና ከጎናችን እንዲቆም ጥሪ እናቀርባለን፡፡

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!

ድል ለአማራ ሕዝብ!

የካቲት 15/2016 ዓ.ም

ግሽ ዓባይ - ጎጃም፤ ኢትዮጵያ

____________________________
Disclaimer: this post and the subject matter and contents thereof - text, media, or otherwise - do not necessarily reflect the views of the 8kun administration.
Post last edited at


[Return][Go to top][Catalog][Nerve Center][Random][Post a Reply]
Delete Post [ ]
[]
[ / / / / / / / / / / / / / ] [ dir / random / 93 / biohzrd / hkacade / hkpnd / tct / utd / uy / yebalnia ]