ከአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ የዕዙን መመስረት አስመልክቶ
የተሰጠ መግለጫ
ታህሣሥ 03/2016 ዓ.ም
ደ/ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ወገልጤና ከተማ
የኢትዮጵያ ማህበረሰባዊ የለውጥ ሂደት ታሪክ ማለትም የሀገረ መንግስት ምስረታና ግንባታ ስርአት፣ ማህበራዊ መስተጋብርና ትስስር ስርአት ፣የምረተ-ስልት ስርዓት እና የእውቀት ምንጭና ስርጸት ስርዓት እንደሚያሰገነዝበው የኢትዮጵያ መገለጫዊ ማንነት የ60ዎቹ ትውልዶች እንዳቀነቀኑትና የአሁናዊ ስርዓት መተክል ሆኖ እያገለገለ እንዳለው የአንድ ማሕበረሰብ ነጠላ ማንነት አልነበረም ፡፡ የልቁንም የሀገራችን መገለጫዊ ማንነት ከሁላችን በሁላችን ለሁላችን ሆኖ ተሰናስሎና ተሸምኖ የተበጀ የወል
ወይም የጋራ ማንነታችን መሆኑን ያስረዳል ፡፡በዚህም
ምክኒያት እኛም የኢትዮጵያ ማንነት የጋራ ማንነት መሆኑን በጽኑ እናምናለን፡፡ ከኢትዮጵያ ማህበረሰቦች አንዱ የሆነው የአማራ ህዝብ በሃገረ-መንግስቱ ምስረታና ግንባታ ሂደት ጉልህ አበርክቶ ያደረገ ታላቅ ህዝብ ነው፡፡ ይህ አበርክቶው ላለፉት 60 ዓመታት በጥላትነት አስፈርጆ ለተካሄደበት እና እየተካሄደበት
ላለው ስም ማጥፋት፣ውንጀላ፣ መሳደድ እና ዘር ማጥፋት አደጋ የዳረገው በለን እናምናለን፡፡
በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መባቻ ጀምሮ በአውሮፓ
እየተቀጣጠለ የመጣው ስር-ነቀል የማህበረሰባዊ የለውጥ ሂደት ማለትም ስርዓተ መንግስት፣ስርዓተ ትምህርት፣ስርዓተ ማህበር እኛ ስርዓተ ምርት ዘግይቶም ቢሆን ወደ ሀገራችን የገባው አሁን ሀገራችን ለምትገኝበት ምስቅልቅል ቀጥተና ምክኒያት መሆኑን እንረዳለን፡፡ከነገስታቱ መንግስታዊ ስርዓት
ጀምሮ የአውሮፓን ማህበረሰባዊ ለውጥ ሂደት ተሞክሮዎች ከሀገራችን ነባር ማህበረሰባዊ ለውጥ ተሞክሮዎች አንጻር ሳይመረምሩና ሳይፈትሹ ለመቅዳት መሞከራቸው ውሎ አድሮ ከሃገራችን ነባር ፍልስፍና ፣መርህና እሴት ጋር ግጭት በመፍጠሩ ሀገሪቱን ለህልውና አደጋ የዳረገ መሆኑን
እንገነዘባለን፡፡ በተለምዶ የ60ዎቹ ትውልድ በመባል የሚታዎቀው የትውልድ ክፍል የአውሮፓን የማህበረሰባዊ የለውጥ ሞዴል የመጀመሪያና የመጨረሻ ብቸኛ አማራጭ አድርጎ መውሰዱ
ብቻ ሳይሆን ነባሩን የኢትዮጵያ ማህበረሰባዊ የለውጥ ሞዴል በጨለማነትና በኋላ-ቀርነት በይኖ መነሳቱ አሁን ሀገሪቱ ለምትገኝበት የህልውና አደጋ የአንበሳው ድርሻ ይይዛል፡፡ ነጻነት፣እኩልነትንና የስልጣን ጥያቄን በማቀንቀን የተነሱት የ60ዎቹ ትውልዶች ጨቋኝና ተጨቋኝ ታሪክና ትርክት
በመፍጠር ለራሳቸውና ማህበራዊ መሰረታችን ነው ብለው ለሚያምኑት ማህበረሰብ ለስነ-ልቦና ስብራትና ለበታችነት ስሜት በመዳረግ ጨቁኖናል ብለው የሚያምኑትን የማህበረሰብ ክፍል ማህበራዊ እረፍት በመንሳት እና ዘሩን ለማሳት የሞከሩት ትግል ባለመሳካቱ ዘር ወደ ማጥፋት ደረጃ እንዲሸጋገሩ የዳረጋቸው፡፡ የአማራ ህዝብ ጥያቄ ሌሎች ማህበረሰቦች ያቀነቀኗቸው ጊዜያቸው ያለፈባቸው ተሞክረው የወደቁ ውጤታቸውም በአውዳሚነት የሚጠናቀቁ የነጻነትና የእኩልነት ጥያቄዎች
አይደሉም ፡፡የአማራ ህዝብ ከምንም ነጻ ለመሆን ከማንም እኩል ለመሆን አይታገልም ነጻነትና እኩልነት የዘመናት እሴት አድርጎ የያዛቸው ስልሆኑ፡፡
የአማራ ህዝብ ጥያቄ የአማራ ብልጽግና እንደሚለው
የአማራ ህዝብ ትግል ጅማሮ ላይ የተነሱ ከወሰንና ከማንነት፣ ከህገ-መንግስት መሻሻል፣በሃገሪቱ ተዘዋውሮ ከመስራትና ከመንቀሳቀስ ጋር የተያያዙ አስተዳደራዊ እና ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን ተሸገሮ፤ በተሳሳተ ፍልስፍና፣ታሪክና ትርክት ተመስርተው እየተፈራረቁ ለስርዓታዊ በደል፣ማህበራዊ እረፍት እና አሁን ለተጋረጠበት የዘር መጥፋት ወይም የህልውና አደጋ የዳረጉ መንግስታዊ ስርዓቶችንና የተመሰረቱበትን መተክላዊ ሃሳብ በመንቀል ሀገራዊ ፍልስፍና እና እሴትን ከዘመናዊ ፍልስፍናና እሴት ጋር ያሰናሰለ በሃቀኛ ታሪክና ትርክት ላይ የተመሰረተ መንግስታዊ ስርዓት ማንበርና በሃገራዊ አንድነት ላይ የተቃጣውን አደጋ በማስቀረት ሀገራዊ አንድነትን ማስጠበቅ ወደ መሆን ተሸጋግሯል፡፡ ፋኖነት ኢትዮጵያ የውስጥም የውጭም ጥላት በአንድነቷና በነጻነቷ ላይ አደጋ በተደቀነበት ወቅት የአደጋ ጊዜ ተጠሪና መውጫ ኃይል የሆነ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ማህበረሰቦች እሴት መሆኑን በጽኑ እናምናለን፡፡ለዚህም ታሪክና አሁን ላይ በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች እየቀረበ ያለው የትግል የአጋርነት ተሳትፎ ህያው ምስክሮች ናቸው፡፡ስለሆነም የአማራ ህዝብን ህልውናን እና የሀገሪቱን አንድነት እየተፈታተነ ያለውን ፈሪና አረመኔያዊ ስርዓት ከመሰረቱ ነቅሎ ለመጣል ከታች በተዘረዘሩት ምክኒያቶች የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ በመመስረት ትግሉ የሚጠይቀውን የአደረጃጀት የአመራርና የማስፈጸም ብቃት ማሳደግ አስፈልጓል፡፡
1. የትግሉ ግብ በማደጉ፡-የአማራ ህዝብ ጥያቄ ሲጀምር አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ የነበሩ ሲሆን ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ ለማስመለስ የሞከረ ቢሆንም ምላሽ ከማግኝት ይልቅ በተቃራኒው ዘር ማጥፋት ነበር የታወጀበት ስሆንም ጥያቄዎቹ መልስ ማግኘት የሚችሉት በስርዓት ለውጥ ደረጃ ወደ ሚደረግ ትግል በማደጉ፡፡
2. የትግሉ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ በማደጉ ፡-በበጥቂቶች የተጀመረዉ ትግል መላዉ አማራን ከማነቃነቅ አልፎ በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያገባቸዉን ሁሉንም ማህበረሰቦች ወደ ማሳተፍ በማደግ ትግሉ የአደጋ ጊዜ መዉጫ ትግል መሆኑን አዉቀዉ በተስፋ የሚጠብቁት በመሆኑ እና ይህንን የህዝብ ንቅናቄ መሸከም የሚችል አደረጀጄት፣ አመራርና የመፈፀም አቅም ማሳደግ አስገዳጅ ስለሆነ፡፡
3. ከፊታችን የሚጠብቀንን ሀገራዊ ሃላፊነት በሚገባ መወጣት ያስችለን ዘንድ ከወታደራዊ ኃይሉ በትይዩ የሲቪል አስተዳደሩን መሸከም የሚችል ኃይል ማዘጋጀት ምቹ ሁኔታ መፍጠር ስለሚያሰፈልግ፡፡
4. የትግሉን ጊዜ ማሳጠር በማስፈለጉ፡- ትግሉ በተራዘመ ቁጥር ይህ ኃላፊነት የማይሰማዉ ስርአት በሀገሪቱ አንድነት እና በማህበረሰቦች መካከል የሚፈጠረዉ አለመተማመን አደጋ ስለሚጨምር ይህን ለመቀነስ ይቻል ዘንድ በተደራጀና በተቀናጀ አካሄድ ትግሉን ማሳጠር አስፈላጊ በመሆኑ፡፡
5. የሌሎች ብሔሮች ወይም ነገዶች በትግሉ የመሳተፍ ፍላጎትና ጥያቄ እየጨመረ በመምጣቱ ለዚህም ምቹ ሁኔታን መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፡፡
6. ትግሉ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱ፡- ይህ መደራጃዉን ፍርሀት ያደረገ አዉዳሚ ስርአት በወሳኝ መልኩ ጦርነቱን ተሸንፏል ብለን እናምናለን፡፡ ለዚህም ተስፋ በቆረጠ ስሜት በምክርቤት ጭምር የሀገሪቱን ግዙፍ ተቋማትና ፕሮጀክቶች በመሸጥና በማቆም ለመዋጋት መወሰኑ እንደ ማስረጃ መውሰድ ይቻላል ፡፡ ይሁንና በወታራዊ አውደ ውጊያ ማሳካት ያልቻለዉን ህልም በሌሎች አዉደ ዉጊያዎች ለማካካስ ርብርብ እያደረገ ይገኛል፡፡ ለአብነት ፋኖን ከህዝቡ ለመነጠል ይረዳኛል ያለዉን አንደኛ ለመንግሰት ተጠሪ የሆነ ቀማኛና ዘራፊ ቡድን በፋኖ ስም በማደራጀት ሁለተኛ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ገንዘብ በመመደብ በትግሉ ዉስጥ የሚሳተፉ ግለሰቦችና ቡድኖችን በጥቅም በመደለል ሶስተኛ በድርድር ስም የስልጣን ፍላጎት ያላቸዉንና የትግሉ እድገት ጋር አብሮ ማደግ ያልቻሉትን ግለሰቦች በመሸንገል አራተኛ የህዝባችንን የመሰረተ ልማት አቅርቦት፣ የሸቀጥ ዝዉዉርን፣ የትምህርትና የጤና አገልግሎት አቅርቦትን፣ የግብርና ቴክኖሎጂ አቅርቦትን ወዘተ… በማስተጓጎል ህዝቡ እንዲማረርና ከትግሉ እንዲነጠል ለማደረግ የሞት ሽረት ርበርብ እያደረገ ይገኛል፡፡ ስለሆነም የትግሉን አደረጃት፣ አመራርና የመፈፀም አቅም በማሳደግ ሊፈጠር የሚችል የትግልክፍተትን በመሙላት ስርአቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ እስከ ወዳኛዉ ማስወገድ በማሰፈለጉ፡፡
7. አለማቀፉ ማህበረሰብ የትግሉን ምንነት፣ አስፈላጊነትና አደረጃጀት የበለጠ በሚረዳዉ ቅርፅና መልክ ማደራጀት አስፈላጊ ሆሞ በመገኘቱ እና በእነዚህና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች ዕዙ ሊመሰረት ግድ ሁኗል፡፡ስለሆነም እኛ በመላው የወሎ ምድር በተለያየ አደረጃጀት እና ቅርጽ የምንቀሳቀስ የፋኖ ሃይሎች ተገናኝተን ባደረግነው ታላቅ ጉባኤ ከትብብር ወደ አንድነት በመሳደግ ዕዙን የመሰረትን መሆኑን ለተከበረው የአማራ ህዝብ፣ ለኢትዮጵያውያን፣በመላው ዓለም ለምትገኙ የትግሉ ደጋፊዎችና የትግል አጋሮቻችን ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው፡፡
በዚህ መሰረት
📌1ኛ.የዕዙ ስያሜ የአማራ ፋኖ በወሎ ዕዝ
📌2ኛ.የዕዙ አደረጃትና ሃላፊነት
የዕዙ ዋና አዛዥ ፋኖ ኮ/ል ፈንታው ሙሃባው
📌የዕዙ ም/አዛዥ ፋኖ ምሬ ወዳጆ
📌የዕዙ አስተዳደር ፋኖ አለምነው መብራቱ
📌የዕዙ ሎጅሰቲክ አዛዥ ፋኖ ኮ/ል ሞገስ ዘገየ
👇የዕዙ የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ፋኖ ሻፊ ሃብታሙ ሆነው
በጉባኤው በአብላጫ ድምጽ መመረጣቸውን እየገለጽን
ትግሉ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱን በማስገንዘብ ከዚህ
በታች ለጠቀስናችሁ አካላት እንደሚከተለው ጥሪያችን
እናስተላልፍላችኋለን ፡፡
ለተከበረው የኢትዮጵያ ህዝብ፡-
ትግላችን ሁለንተናዊ የህልውና አደጋ የተጋረጠበትን የአማራ
ህዝብ መታደግና የሀገራችን አንድነት እና ሉዓላዊነት
ማስጠበቅ መሆኑን ተገንዝበሃል ብለን እናምናለን ፡፡ለዚህም
ለትግሉ ተሳትፎህንና አጋርነትህን በማሳየት
አረጋግጠሃል፡፡ስለሆነም በስሁት ፍልስፍና፣ታሪክና ትርክት
ተመስርቶ የጋራ ማንነታችን ለማጥፋትና ሀገራችንን
ለመበተን አበክሮ እየሰራ ያለውን ፈሪና ድንጉጥ መንግስታዊ
ስርዓት ከኢትዮጵ ጫንቃ ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ
አሽቀንጥሮ ለመጣል የምናደርገውን ትግል የበለጠ
ተሳትፎህንና አበርክቶህን እንድታጠናክር አጥብቀን
እንጠይቃለን፡፡
ለተከበረው የአማራ ህዝብ፡-
ሁሉን አቀፍ መንግስታዊ በድልንና አሻጥርን ተቋቁመህ
ስርዓቱን ለመንቀል የምናደርገውን ትግል
በልጆችህ፣በገንዘብህና በስነ-ልቦናህ እየከፍልህ ያለውን
መስዋዕትነት እንደ በፊቱ ሁሉ በታሪክ ፊት የምትከብርበትና
የምትኮራበት መሆኑ ጥርጥር የለውም ፡፡ስለሆነም ትግሉ
በአጭር ጊዜ ተቋጭቶ ማህበራዊ ዕረፍት ታገኝ ዘንድ
ለምናደርገው ትግል የተለመደውን ሁለንተናዊ ድጋፍና
ትብብር እንዳይለየን እንጠይቅሃለን፡፡
ውጭ ለምትኖሩ የትግሉ አጋርና ደጋፊዎቻችን፡-
ሙያችሁን ፣ገንዘባችሁንና ጊዜችሁን ሰውታችሁ
ያለመሰልቸት የምታደርጉት ተጋድሎ ሁሉ በሃገራችን
የለውጥ ታሪክ አይረሴና ጉልህ አሻራ መሆኑን በፍጹም
ልባችን እናምናለን፡፡ስለሆነም ትግሉ የበለጠ ቅርጽና መልክ
ኑሮት በቋፍ ላይ ያለችውን የጋራ ሀገራችን እንታደግ ዘንድ
በመካከላችሁ የሚስተዋሉ ጥቃቅን መጓተቶችን በመቅረፍ
የተለመደውን የትግል አጋርነታችሁን እንድታጠናክሩ ጥሪ
እናስተላልፋልን፡፡
በየክፍለ-ሀገሩ እየተዋደቃችሁ ላላችሁ የትግል ጓዶቻችን፡-
የትግሉ ወሳኝ ምዕራፍ መድረሱና ለህዝባችን እና ለሀገራችን
ትግሉን በአጭር ጊዜ የመጠናቀቅ አስፈላጊነት አጣዳፊና
ወቅታዊ መሆኑን ተገንዝበን ከትብብር ወደ አንድነትና
ውህደት ለመምጣት የምናደርገው ርብርብ የተሳለጠና
የተቃና እንዲሆን ፤ ጥላት ይህ አንድነት እውን እንዳይሆን
በመካከላችን እያደረገ ያለውን አሻጥር ወደ ጎን በመተው
ወደ አንድነትና ውህደት በፍጥነት እንድንመጣ በተሰው
ሰማዕታት ወንድሞቻችንና በአማራ ህዝብ ስም ወንድማዊ
ጥሪያችን እናስተላልፋልን፡፡
ለመከላከያ ሰራዊት፡-
ከሀገር ደጀንነትና ጠባቂነት ክብርህ ወደ ቡድንና ግለሰብ
ስልጣን ጠቢቂነት አዋርዶ ፤ንቃትህንና ህሊናዊ ሁኔታህን
በማራከስ፤መስመራዊ መኮንኖችህንና የበላይ አመራሮችህን
በጥቅም በመደልል ፤ዓላማ በሌለውና የኩራትህ ምንጭ
ከሆነው ህዝብህ ጋር ደምህን እንድታፈስና አጥንትህን
እንድትከሰክስ ፣ተዋርደህ እንድትበተን በማድረግ ስርዓቱ
ሀገር አፍርሶ ሀገር ለማዋለድ ለያዘው ፕሮጀክት
ማስፈጸሚያ እያደረገህ መሆኑን ተገንዝበህ ሀጊሪቱን ከብተና
ለመታደግ የምናደርገውን ትግል እንድታግዝ ሀገራዊ ጥሪ
እናቀርብልሃለን፡፡
ለአማራ ብልጽግና ፡-
የአማራ ህዝብ ጥያቄ አንተ እንደምትለው የማንነትና
የወሰን፣የህገ-መንግስት መሻሻልና መፈናቀልና መሰደድ እንዲቆም የሚል አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች የተሸገረ እና ጥያቄዎቹ መልስ የሚያገኙት መንግስታ ስርዓቱና ስርዓቱ የተመሰረተበትን አስተሳሰብ ከስሩ መንቀል ወደ ሚል ተሸጋግሯል፡፡ስለሆነም ሳይመሽብህ የተላላኪነትና የባንዳነት አመልህን ጥለህ አይቀሬውንና አሸናፊውን የአማራ ህዝብ ትግል ከማጓተትና ከማደናቀፍ እንድትታቀብ በድጋሜ እናስጠነቅቅሃለን፡፡ ‹‹እየመጣን ነው››
የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ
ማሳሰቢያ
በእዚህ የዕዝ አደረጃጀት ውስጥ ለመደራጀት የምትፈልጉ ነባርም ሆናችሁ አዲስ የምትመሰረቱ የትግል ሃይሎች በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ መቀላቀል የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።